ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ
ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ
ለእግዚአብሔር አቅርቡ። ሮሜ 6፡13
ብልቶቻችን
ከአመፃም ከፅቅድቅም ገለልተኛ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ብልቶቻችን ወይ አመፃ ያልፍባቸዋል ወይ ፅድቅ ያልፍባቸዋል፡፡ ብልቶቻችን ፅድቅ
ካለፈባቸው ሁለት ነገር ባንዴ ሊያልፍባቸው ስለማይችል አመፃ ሊያልፍባቸው አይችልም፡፡
ከብርጭቆ
ውስጥ ውሃውን ካወጣነው ከመቀፅበት በአይን የማይታይ አየር ብርጭቆውን ይሞላል፡፡ ውሃም አየርም የሌለው ገለልተኛ ሊሆን አይችልም፡፡
አንድ
ነገርን ላለማድርግ አንድ ነገርን ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡ ብልቶቻችንን የአመፃ የጦር እቃ አድርጎ ላለማቅረብ ከምንታገል ይልቅ ብልቶቻችንን
የፅድቅ የጦር እቃ አድርጎ ማቅረብ ከመቀፅበት የአመፃ የጦር እቃ እንዳይሆኑ ውጤታማ ያደርገናል፡፡
ፅቅድ
ያለፈበባቸው ብልቶቻችን አብሮ አመፃ ሊያልፍባቸው አይችልም፡፡
ስለዚህ
አመፃ እንዳያልፍበት ከፈለግን በጊዜ በፅድቅ ቦታ ማስያዝ አለብን፡፡ በፅድቅ ቦታውን የያዘ ብልት ለአመፃ ትርፍ ቦታ የለውም፡፡
የውሃ
ማስተላለፊያን ቧንቧ ሙቅ ውሃ ካስተላለፈ ቀዝቃዛ ውሃ ለማስተላለፍ ቦታ እንደማይቀረው ሁሉ መንፈሳዊም ነገር እንዲሁ ነው፡፡ በእለት
ተእለት ህይወታችን የእግዚአብሄር ቃል የሚለውን በማድረግ የእግዚአብሄር ቃል የማይለውን አለማድርግ እንችላለን፡፡ የእግዚአብሄርን
ቃል በመታዘዝ አለመታዘዝን እንበቀላለን፡፡
መታዘዛችሁም
በተፈጸመች ጊዜ አለመታዘዝን ሁሉ ልንበቀል ተዘጋጅተናል። 2ኛ ቆሮንቶስ 10፡6
ሰው
ብልቶቹን የአመፃ መጠቀሚያ አድርጎ ላለማቅረብ ከአመፃ ጋር ከመጋደል ይልቅ የፅድቅ መጠቀሚያ ማድረግ በተዘዋዋሪ ውጤታማ ያደገዋል፡፡
ሰው ብልቶቹን የአመፃ የጦር እቃ አድርጎ ላለማቅረብ የሚያዋው አስቀድሞ የፅድቅ የጦር እቃ አድርጎ ማቅረብ ነው፡፡
ብልቶቹን
የፅድቅ የጦር እቃ አድርጎ ያቀረበ ሰው ብልቶቹ የአመፃ የጦር እቃ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ብልቶቹ የፅድቅ የጦር እቃ ያልሆኑ ሰው ግን
ወደደም ጠላም ብልቶቹ የአመፃ የጦር እቃ ላይሆኑ አይችሉም፡፡
ሰው
ራሱን ለሃጢያት ለመስጠት አስቀድሞ ራሱን ለፅድቅ መስጠት አለበት፡፡ ሰው ራሱን ለፅድቅ ሳይሰጥ ለሃጢያት አልስጥ ብሎ ቢመኝ አይሆንም፡፡
ሰው ወይ የፅድቅ መጠቀሚያ ይሆናል ወይም ደግሞ የሃጢያት መጠቀሚያ ይሆናል፡፡ ሰው ከፅድቅና ከሃጢያት መጠቀሚያነት ገለግልተኛ ሊሆን
አይችልም፡፡
ሰው
እግዚአብሄርን ለማስደሰት የእግዚአብሄርን ቃል ማንበብና ማሰላለስ በእግዚአብሄር ቃል አእምሮውን ማደስ አለበት፡፡
የእግዚአብሔር
ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ
ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2
ሰው
ግን በእግዚአብሄር ቃል አእምሮውን ለማደስ ራሱን ካልሰጠ የሰይጣንን ሃሳብ አላስተናግድም ብሎ ቢፍጨረጨር አይችልም፡፡ ሰው አእምሮው
በእግዚአብሄር ቃል ካልተሞላ ወደደም ጠላም ከእግዚአብሄር ቃል ውጭ በሆነ ነገር ይሞላል፡፡
ሰው
ራሱን ለእግዚአብሄር ጥበብ ካልሰጠና የእግዚአብሄርን ጥበብ ካልፈለገ ወደደም ጠላም የምድርን ጥበብ ሲያስተናገድ ይኖራል፡፡
ይህ
ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ
በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ
ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት። ያዕቆብ 3፡15-17
ሰው
እግዚአብሄርን ለማገልገል ራሱን ካልለየ አለምንና ሰይጣንን ያገለግላል፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ካልወደደ አለምን ይወዳል፡፡ ሰው አለምን
ላለመውደድ ከሚፍጨረጠጨር ይልቅ እግዚአብሄርን ቢወድ ፍሬያማ ይሆናል፡፡
ዓለምን
ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ
እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም። 1ኛ ዮሃንስ 2፡15-16
ብልቶቻችሁንም
የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር
አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ። ሮሜ 6፡13
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #እምነት #የዓመፃየጦርዕቃ #የጽድቅየጦርዕቃ #አቅርቡ #አታቅርቡ #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #መዳን #ማድረግ #መስዋእት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ