ባህሪ
ያለው ሰው ከሃያል ሰው ይሻላል፡፡ ምክኒያቱም ሰው ሃየል ቢኖረው እንኳን በአግባቡ የሚጠቀምበት ራስን መግዛት ከሌለው ከጥቅሙ ይልቅ
ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ስለዚህ ነው ከሃይል ይልቅ ባህሪ ይሻላል የሚባለው፡፡
ትዕግሥተኛ
ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል። ምሳሌ 16:32
የእግዚአብሄርን አብሮነት የሚደሰትበት ሰው ባህሪውን
ለመስራት የሚተጋ ሰው ነው፡፡
ሕይወትን
ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ ከክፉ ፈቀቅ ይበል፥ መልካምንም
ያድርግ፥ ሰላምን ይሻ ይከተለውም፤ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡10-11
የተጠራነው የክርስቶስን ባህሪ እንድንለብስ ነው፡፡
እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ፤ እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ፤ በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት። ቆላስይስ ሰዎች 3፡12-14
ተከታተሉት የተባልነው የክርስቶስን ባህሪ ነው፡፡
አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡11
ለሌሎችም መልካም ምሳሌ በመሆን ሌሎችን ለክርስቶስ
የምንማርከው በባህሪ ነው፡፡
ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው።1ኛ ጢሞቴዎስ 4፡11-12
መከራን በደስታ የምንታገሰው እና በመከራ የምንመካው
እግዚአብሄርን የማያስደስተውን ባህሪያችንን ስለሚገርዘው ነው፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፥
ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤ ሮሜ ሰዎች 5፡3-4
የጤናማ ትምህርት ውጤት ባህሪን መገንባት ስለሆነ
ነው፡፡ ፀጋን የተረዳ ሰው በፀጋ /በሚያስችል የእግዚአብሄር ሃይል/ ባህሪውን ይገነባል፡፡ እለት ተእለት እግዚአብሄርን ለመምሰል
ራሱን ያስለምዳል፡፡
አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር። ሽማግሌዎች ልከኞች፥ ጭምቶች፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ በእምነትና በፍቅር በመጽናትም ጤናሞች እንዲሆኑ ምከራቸው፤ እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ
የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤ ቆነጃጅትም የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ፥ ባሎቻቸውን የሚወዱ፥ ልጆቻቸውን የሚወዱ፥ ራሳቸውን
የሚገዙ፥ ንጹሖች፥ በቤት የሚሠሩ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው። ጎበዞችም እንዲሁ ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው።
የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር፥ በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግህ ምሳሌ የሚሆን ራስህን አሳይ፤
በትምህርትህም ደኅንነትን፥ ጭምትነትን፥ ጤናማና የማይነቀፍ ንግግርን ግለጥ። ባሪያዎች ስለ መድኃኒታችን ስለ እግዚአብሔር የሚሆነውን
ትምህርት በሁሉ ነገር ያስመሰግኑ ዘንድ፥ ለገዛ ጌቶቻቸው እንዲገዙ በሁሉም ደስ እንዲያሰኙ፥ ሳይቃወሙና ሳይሰርቁም በጎ ታማኝነትን
ሁሉ እንዲያሳዩ ምከራቸው።ቲቶ 2፡1-10
ክርስቲያናዊ ባህሪ ከብዙ ባለጠግነት ይሻላል፡፡
በጠማማ መንገድ ከሚሄድ ባለጠጋ ያለ ነውር የሚሄድ ድሀ ይሻላል። ምሳሌ 28፡6
መልካም ስም ከብዙ ባለጠግነት ይሻላል፥ መልካምም ሞገስ ከብርና ከወርቅ ይበልጣል። ምሳሌ 22፡1
ክርስቶሳዊ ባህሪ ወደ ህይወት የሚመራ መሪ ነው፡፡
አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው፤ እውነተኛ ሚዛን ግን ደስ ያሰኘዋል። ቅኖች ቅንነታቸው ትመራቸዋለች፤ ወስላቶችን ግን ጠማማነታቸው
ታጠፋቸዋለች። መጽሐፈ ምሳሌ 11፡1፣3
መልካ
ባህሪ አስተማማኝ መከር ያስገኛል፡፡
ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት። ገላትያ 6፡9
ቅዱሳት መፅሃፍት የተሰጡት በክርስቶስ ባህሪ ሊያሳድጉን
ነው፡፡
የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና
ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16-17
ለባህሪያችን መሰራት የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ
እግዚአብሄር ሰጥቶናል፡፡
የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ 2ኛ ጴጥሮስ 1፡2-3
ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም
ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል። ምሳሌ 16:32
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ
#ፍቅር #ሰላም
#ደስታ #ዘር
#ባህሪ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#የእግዚአብሄርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት
#የዋሃት #ራስንመግዛት
#ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment