ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም፥ ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው። ገላትያ 4፡1-2
·
ከውጭው ይልቅ ስለ ውስጡ ስለልባችን
ማሰብ
ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡4
·
ለሰው ያለ ትልቅ ክብር
ሰው ማደጉ የሚታወቀው
ለሰው ያለው ክብር ሲጨምር ነው፡፡ በተለይ ሰውን ስላለው ነገርና ስለሆነውስ ነገር ሳይሆን ስለሰውነቱ ብቻ መናክበር ከቻለ በሳል
ሰው ነው ይባላል፡፡
ዝቅተኛ ኑሮ ወይም ዝቅተኛ ሥራ ለመሥራት ፍቀዱ ውስጥ ካሉ ጋር አብራችሁ ለመሆን
ፍቀዱ እንጂ አትኵራሩ፤ በራሳችሁም አትመኩ። ሮሜ 12፡16
·
ሰዎችንና ነገሮችን የመተው
ችሎታ
የበደሉንን ለመተው
ይቅር የማለት ችሎታ ክርስያናዊ ብስለትን ይጠይቃል፡፡ የስኬት ምንጭ እግዚአብሄር
መሆኑን አውቆ ለእድገት ከሰው ጋር አለመከራከር አለመጣላት፡፡
የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ። ዕብራውያን 10፡34
·
ቁሳቁስን ቀለል አድርጎ መመልከትና
ለምድራዊ ነገር አለመንገብገብ
ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤ ወደ ዓለም ምንም እንኳ አላመጣንምና፥ አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን፥ እርሱ ይበቃናል። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፡6-8
·
በዝቅታ በእግዚአብሄር መታመንና
በምድር ራስን እንደ እንግዳ መቁጠር
ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ ዕብራውያን 11፡9
በሥጋ ስናድር ከጌታ
ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡6-7
·
የዘላለም ህይወት እይታ
በጌታ ያደገ ሰው ማንኛውንም
ውሳኔ የሚወስነው ለዘላለም መንግስት ካለው ጥቅም አንጻር ነው፡፡ በሳል ሰው ምንም ነገርን የሚመዝነው በዘላለም እይታ ነው፡፡
እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥
ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ 3፡1-2
መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ ፊልጵስዩስ 3፡19-20
·
ከከንቱ ውድድር እና ፉክክር
እስራት ነፃ መውጣት
ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም። 2ኛ ቆሮንቶስ 10፡12
·
ከምንም ነገር ስለ አላማ ማሰብ
በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ። ፊልጵስዩስ 3፡14
የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡28
·
ካለ እግዚአብሄር ምሪት ለመሄድ
አለመቸኮል
እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡27
·
ሌላውን በትህትና መመልከት
ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። ፊልጵስዩስ 2፡3፣5
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ
#ፍቅር #ሰላም
#ደስታ #ትህትና
#ባህሪ #ምሪት #ዘላለም #መተው #ልብ #ፉክክር #ቁሳቁስ #መታመን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሄርህይወት
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት #የዋሃት #ራስንመግዛት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment