እግዚአብሔርም ለሰሎሞን እጅግ ብዙ ጥበብና ማስተዋል በባሕርም ዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት ሰጠው። 1ኛ ነገሥት 4፡29
በህይወቴ እንዲኖረኝና ይበልጥ እንዲኖረኝ የምፈልገው
የልብ ስፋት ነው፡፡
የልብ ስፋት ግን ለምን አስፈለገ
1.
ከልባችን ስፋት በላይ በምንም
ነገር መስፋት ስለማንችል ነው፡፡
አገልግሎታችን እንዲበዛ
ያለንን አገልግሎት የሚይዝ ሰፊ ልብ ያስፈልገናል፡፡ ሃብታችን እንዲበዛ ያንን ማስተዳደር ብቃት ያለው ሰፊ ልብ ያስፈልገናል፡፡
አሁን የደረስንበት ደረጃ የልባችን ስፋት ደረጃ ነው፡፡ ምንም ብንመኝ ከልባችን ስፋት ደረጃ በላይ አናድግም፡፡ እያንዳንዱን ሰው
እንደ አቅሙ ይዘን ከእያንዳንዱ ውስጥ የተሻለ ነገር ለማውጣት ሰፊ ልብ ይጠይቃል፡፡ ሃላፊነታቸን መብዛት ካለበት ልባችን መጀመሪያ
መስፋት አለበት፡፡
ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። ማቴዎስ 25፡15
2.
ሰዎች የተለያዩ ስለሆኑ ነው፡፡
ሰዎች ሁሉ እኛን አይመስሉም፡፡
እኛን ደረጃ መዳቢ አድርገንም ሌላው ሰው ሁሉ ራሱን ትቶ እኛን እንዲመስል ከፈለግን አይቻልም፡፡ ይልቁንም ሁሉንም ሰው እንደ ደረጃውና
እንደዝንባሌው መረዳትና መቀበል የሚችል ሰፊ ልብ ያስፈልገናል፡፡
ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች
ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም
ደስ እንደማይላቸው፥ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡30-31
3.
ሰፊ ልብ የሚጠይቀው ሁኔታዎች
ስለሚለዋወጡ ነው፡፡
ሁኔታዎች ይለዋወጣሉ፡፡
አሁን እናገኛለን ሌላ ጊዜ አናገኝም፡፡ አሁን እናተርፋለን ሌላ ጊዜ ደግሞ ልንከስር እንችላለን፡፡ ይህ እኔ ላይ አይሆንም ያለነው
ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን አንወጣለን ሌላ ጊዜ ደግሞ እንወርዳለን፡፡ ይህንን ተለዋዋጭ አለም ተቋቁመን ማለፍ የምንችለው በሰፊ
ልብ ብቻ ነው፡፡ ሰፊ ልብ ከሌለን ከደረሰበን ነገር አንፃር እንደገና መኖር ሊያስፈራን ይችላል፡፡
ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡4-6
4.
ሰፊ ልብ ያስፈለገው ሰዎች
ስለሚለወጡ ነው፡፡
ሰዎች በተለያየ ምክኒያት
ይለወጣሉ፡፡ አይክዱንም ያልናቸው ሰዎች ሊክዱን ይችላሉ፡፡ ሰፊ ልብ ከሌለን ተመልሰን ሌላ ሰውን ማመን ያቅተናል፡፡ ሰውን ካላመንን
ደግሞ ውስን እንሆናለን፡፡ የሌሎችን ህይወት መቆጣጠር አንችልም፡፡ ማድረግ የምንችለው የተሻለ ነገር ልባችንን ማስፋት ብቻ ነው፡፡
ከእግረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፥ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ? በሰላምም ምድር ታምነህ ብትቀመጥ፥ በዮርዳኖስ ትዕቢት እንዴት ታደርጋለህ? ኤርምያስ 12፡5
5.
ሰፊ ልብ ያስፈለገው እውቀት
ሁሉ ስለሌለን ነው፡፡
አንዳንድ ጊዜ የምናውቀውን
እውቀት ሁሉ ወደጎን አድርገን ሁሉን በሚያውቀው በእግዚአብሄር ላይ መታመን ይገባናል፡፡ በሚያውቁት እውቀት ለመሄድ ሰፊ አእምሮ
ሲጠይቅ በማይገባንና በማንረዳው መንገድ ለመሄድ ሰፊ ልብ ይጠይቃል፡፡
አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። ዕብራውያን 11፡8
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #እምነት
#ሃሳብ #ልብ
#ዋጋ # #አማርኛ
#ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #ልብ
#እምነት #ቃል
#አእምሮ #ማደስ
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment