ሰው ሁሉ ነገር ኖሮት እሳቱ የመውጣት የመውረስ
እሳቱና መቀጣጠሉ ከጠፋ ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ሰው ሁሉ ነገር ኖሮት ሃሞቱ ከፈሰሰ ለእግዚአብሄር መንግስት ምንም ነገር ማድረግ
አይችልም፡፡ ሰው እምቅ ጉልበት ኖሮት እሳቱ ግን ከሌለው ከንቱ ነው ለጌታ ስራ ምንም አይጠቅምም፡፡
ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤ ሮሜ 12፡11
እስከመጨረሻው የሚዋጉ እጅ የማይሰጡ እሳቱና መቀጣጠሉ
ያላቸው ሰዎች ያስፈልጋሉ፡፡
ሙሴም በላከኝ ጊዜ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬ ጕልበታም ነኝ፤ ጕልበቴም በዚያን ጊዜ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ዛሬ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጉልበቴ ያው ነው። አሁን እንግዲህ በዚያን ቀን እግዚአብሔር የተናገረውን ይህን ተራራማ
አገር ስጠኝ፤ አንተ በዚያ ቀን ዔናቃውያን ታላላቆችና የተመሸጉ ከተሞችም በዚያ እንዳሉ ሰምተህ ነበር፤ ምናልባት እግዚአብሔር ከእኔ
ጋር ይሆናል፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረኝ አሳድዳቸዋለሁ። ኢያሱ 14፡11-12
እሳትን
የሚጭረው የሚያነሳሳውና የሚያስቀጥለው የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡
እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል፥ አይጠፋም፤ ካህኑም ማለዳ ማለዳ እንጨት ያቃጥልበታል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በዚያ ላይ ይረበርባል፤ በዚያም የደኅንነትን መሥዋዕት ስብ ያቃጥላል። ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤ አይጠፋም። ዘሌዋውያን 6፡12-13
በውኑ
ቃሌ እንደ እሳት፥ ድንጋዩንም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን? ይላል እግዚአብሔር፡፡ ኤርምያስ 23፡29
እሳትን
ደግሞ የሚያዳፍነው አንዱ ነገር ፍርሃት ነው፡፡ ሰው ሲፈራ እሳቱ ይዳፈናል፡፡
ስለዚህ ምክንያት፥ እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው፥ እጆቼን በመጫኔ በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ። እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና። 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡6
ሌላው ከፈቀድንለት እሳትን የሚያዳፍነው ነገር
መከራ ነው፡፡ በህይወት ያለ ተግዳሮት አላማው ድፍረታችንን መምታትና እጅ እንድንሰጥ ማድረግ ነው፡፡
እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፥ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፡8
ስለዚህ ነው የእግዚአብሄር ቃል ድፍረታችሁን አትጣሉ
ብሎ የሚያዘው፡፡
እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ። ዕብራውያን 10፡35
ሌላው እሳታችንን ጠብቀን እንድንቆይ የሚያደርገን
የወንድሞች ህብረት ነው፡፡
ለፍቅርና
ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን
እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ። ዕብራውያን 10፡24-25
ሌላው
የአገልግሎት እሳታችንን ጠብቀን እንድንዘልቅ የሚያደርገው ኢየሱስን ብቻ መመልከት ነው፡፡
እንግዲህ
እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም
ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል
ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ዕብራውያን 12፡1-2
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #እሳት #ህብረት #ቃል #መቀጣጠል #ክብር #አገልግሎት #መዋረድ #መርካት #ፀጋ #እውቀት #ኢየሱስንተመልክተን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #እምነት #ታላቅነት #ማገልገል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment