Popular Posts

Follow by Email

Friday, June 2, 2017

የፀጋው ክብር

ፀጋ ነፃ ስጦታ ነው፡፡ ፀጋ በነፃ ከእግዚአብሄር የሚሰጥ ችሎታ ነው፡፡ ፀጋ የሚያስችል ሃይል ነው፡፡ ፀጋ የሚያስልች ብቃት ነው፡፡ ፀጋ የሚያስችል ችሎታ ነው፡
ፀጋ እግዚአብሄር በህይወታችን እንድንሆን የፈለገውን እንድሆን የሚያስችል ሃይል ነው፡፡
ፀጋ በህይወታቸነ እንድናገኝ የፈለገው ነገር ሁሉ እንድናገኝ የሚያስችል የእግዚአብሄር ድጋፍ ነው፡፡
ፀጋ እግዚአብሄር በህይወታችን እንድናደርገው የፈለገውን ነገር ሁሉ እንድናደርግ የሚያስታጥቀን ችሎታ ነው፡፡
የዳንነው በፀጋው እንደመሆኑ መጠን ለእግዚአብሄር የምንኖረው በፀጋው እንጂ በስጋ ክንድ አይደለም፡፡ የዳንነው በራሱ ችሎታና አሰራር እንደመሆኑ ለእግዚአብሄር እንድ ነገር ካደረግንለት በራሱ ችሎታ ነው፡፡ የዳንነው በፀጋ እንደመሆኑ መጠን እግዚአብሄር የሚፈልገውን ነገር ከሆንንለት በእግዚአብሄ የሚያስችል ችሎታ ነው እንጂ በራሳችን ጉልበት አይደለም፡፡
ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡30-31
ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ ቲቶ 2፡11-14
1.      የዳነው በፀጋው ነው፡፡
ወደ እግዚአብሄር መቅረብ እንድንችል እግዚአብቭጌር ሞገሱን ሰጥቶናል፡፡ ጠላቶች የበነበረነውን ልጆች እንድባል ፀጋው አብቅቶናል፡፡
2.     የተቀደስነው በፀጋው ነው፡፡
በቅድስና ለእግዚአብሄር የምንለየው በእግዚአብሄር ችሎታ ነው፡፡ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞትን የምንክደው በእግዚአብሄር ችሎታ ነው፡፡ ቲቶ 2፡12
3.     ራሳችንን የምንገዛው በፀጋው ነው
የስጋን ክፉ ምኞት ተቋቁመን ራሳችንን በመግዛት በቅድስና ለእግዚአብሄር ብቻ የምንኖረቅው በራሳችን ችሎታ አይደለም በፀጋው ነው፡፡ ቲቶ 2፡12
4.     እግዚአብሄርን የምንመስለው በፀጋው ነው፡፡
እግዚአብሄርን ለመምሰል የሚያስችል የእግዚአብሄር ሃይል ይጠይቃል፡፡ ካለ እግዚአብሄር ሃይል እግዚአብሄርን መምሰል እንችልም፡፡ የእግዚአብሄር ችሎታ በእኛ ውስጥ ሲሰራ ነው እግዚአብሄርን መምሰል የምንችለው፡፡ ቲቶ 2፡12
5.     በአለም ውጣ ውረድ የምንበረታው በፀጋው ነው፡፡
አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤ አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 6፡1፣3-5
6.     እግዚአብሄርን የምናገለግለው በፀጋው ነው
ስለዚህ ምክንያት ምሕረት እንደ ተሰጠን መጠን ይህ አገልግሎት ስላለን አንታክትም። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡1
7.     የሚጠሉንን የምንወደው ፣ የሚረግሙንን የምንመርቀውና ለሚያሳድዱን የምንፀልየው በእግዚአብሄር ፀጋ ነው
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ ማቴዎስ 5፡44-45
8.     ሌሎችን የምናገለግለው በእግዚአብሄር ችሎታ ነው
ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤ 1ኛ ጴጥሮስ 4፡10
9.     እግዚአብሄር የጠራንን አገልግሎት ሁሉ የምናደርገው በፀጋው ነው
የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ ጴጥሮስ 1፡2-3
10.    በድካም የምንበረታው በእግዚአብሄር ማስቻል ነው
ከድካማችን አልፈን የእግዚአብሄርን አላማ በህይወታችን የምናስፈፅጽመው በእግዚአብሄር ሃይል ነው፡፡
ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡7
ኢየሱስ ነፍሱን አሳልፎ የሰጠው የእኛን ሃጢያት ይቅር ሊለን ብቻ ሳይሆን ለእግዚአብሄር የሚጠቅሙ ሰዎች አድርጎ በራሱ ችሎታ ሊያስታጥቀን ነው፡፡ ለመዳን በፀጋው ጀምረን መሃል ላይ ተቀብለነው በጉልበታችን እንጨርስም፡፡ የእግዚአብሄር ፀጋ መዳናችን ላይ አያበቃም፡፡ የእግዚአብሄር ፀጋ ከመዳናችን ጀምሮ ወደሰማይ እስከምንሄድ ደረስ አንዳች ትርጉም ያለው ነገር ካደረግን በፀጋው ብቻ ነው፡፡
መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ቲቶ 2፡14
ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። ሮሜ 11፡36
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #ብቃት #የእግዚአብሄርችሎታ #የእግዚአብሄርሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ፅድቅ #እግዚአብሄርንመምሰል #ራስንመግዛት #ልብ

No comments:

Post a Comment