Popular Posts

Sunday, June 18, 2017

የአባትነት ጣእም

ማንኛውንም ትውልድ በዋነኝነት የሚሸከሙት አባቶች ናቸው፡፡ የአባቶች ጥንካሬ የትውልዱን ጥንካሬ ይወስናል፡፡ የአባቶች ስስትና ራስ ወዳድነት ትውልዱን ያዳክማል፡፡
በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው ድክመት ወደኋላ ተመልሶ ቢጠና አስተዋፅኦ ያደረገው የቀደመው ትውልድ ድክመት ነው፡፡
ራሳቸውን የሚሰጠዩ አባቶች ሲጠፉ ትውልድ ጥላ በማጣት ይሰቃያል፡፡ ልጆች ተወልደው ይበተናሉ፡፡ ልጆች ተወልደው ስለመወለዳቸው ሃላፊነት የሚወስድ ስለሌለ በትውልዱ ላይ መጥፎ ስሜት ይዘው ያድጋሉ፡፡ ስለመወለዳቸው ሃላፊነት የሚወስድ አባት በሌለበት ልጆች ተወልደው ከአባቶቻቸው አካሄድ ብቻ ሃላፊነት አለመውሰድን ይማራሉ፡፡  
ራስ ወዳድ አባቶች ባሉበት ልጆችና የሚቀጥለው ትውልድ ይሰቃያል፡፡ አባቶች ሃላፊነት የሚሰማቸው ሲሆን ትውልዱ ማንኛውንም ችግር ይቋቋማል ይለመልማል፡፡
ልጆቻቸውንና ህብረተሰቡን ስብስብ አድርገው የሚይዙ ትጉህ አባቶች ካሉ ደግሞ ህዝብ በሰላም ይወጣል ይገባል፡፡
ክፉውን ክፉ ብለው የሚቃወሙ መልካሙን የሚያበረታቱ አባቶች ሲኖሩ ህዝብ ክፋት መቋቋም ያቅተዋል፡፡  
ራሳቸውን ብቻ የሚሰሙ ለመማርና ለመለወጥ ፈቃደኛ ያልሆኑ አባቶች ሲኖሩ የሚማር ልብ የማጣታቸው ውጤት በትውልዱ ላይ ይንፀባረቃል፡፡ ለልጆቻቸው የትእቢትና የንቀት መጥፎ ምሳሌ ይሆናሉ፡፡  
አሁን የሚታየው የትውልድ ድክመት በዋነኝነት በጥቅም ላይ ብቻ በሚያተኩሩ ሃላፊነትን በሚዘነጉ አባቶች የመጣ ነው፡፡
በቤተሰብ ላይ ችግር ሲመጣ የሚጋፈጡ ራሳቸውን መስዋእት የሚያደርጉ አባቶች ራስ ወዳድ ላልሆኑ ልጆች መልካም ምሳሌ  ይሆናሉ፡፡ ራስ ወዳድ ያልሆኑ አባቶች ራስ ወዳድ ያልሆኑ ልጆችን ለማፍራት እቅጣጫንና ጉልበትን ያካፍላሉ፡፡
ችግር ሲመጣ የሚፈረጥጡና ስለ ችግሩ ሃላፊነት የማይወስዱ አባቶች ሳያውቁት ተጠያቂነትን ለሚሸሽ ልጥምጥ ትውልድ መጥፎ ምሳሌ ይሆናሉ፡፡
ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል? 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፡4-5
መልካም የአባቶች ቀን
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ወላጅ #ፍቅር #አባት #እርማት #ጥንካሬ #አባትነት #ተግሳፅ  #መሪ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment