Popular Posts

Thursday, June 15, 2017

አባቶች እንሁን

ብዙ ጊዜ በቤተክርስቲያን ህፃናት ማሳደጊያ ለመጎብኘትና እርዳታ ለማድረግ እድል አጋጥሞን ነበር፡፡ አንድ እርዳታ በሰጠንበት ህፃናት ማሳደጊያ የገጠመኝን ላካፍላችሁ፡፡
እርዳታውን ከመስጠታችን በፊት የህፃናት ማሳደጊያው ሰራተኞች ብናገኝ ብለው የሚመኙትን ዝርዝር እንዲሰጡን ጠይቀናቸው ነበር፡፡ በጥያቄያችን መሰረት የጎደላቸውንና ቢያገኙ ደስ የሚላቸውን ቁሳቁሶች ዝርዝር ሰጥተውን ነበር፡፡ የወሰድንላቸው እርዳታ የምኞታቸውን ዝርዝርና ከዚያም በላይ ነበር፡፡ በዚያ ምክኒያት በጣም ነበር የተደሰቱት፡፡
ከማሰገኑን በሁኋላ ግን ሌላም ማድረግ የምትችሉት ነገር አለ አሉን፡፡ ምንድነው ማድረግ የምችልው ብለን ስንጠይቅ፡፡ ፍላጎታቸውን እንዲህ በማለት አስረዱን፡፡
እነዚህ ልጆች በወላጆቻቸው የተተዉ ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ልጆች ናቸው፡፡ አብዛኛው እዚህ የምንሰራውና እንደእናት የምንከባከባቸው ሴቶች ነን፡፡ ነገር ግን እነዚህ ልጆች በህይወታቸው የአባት ምሳሌ ያስፈልጋቸዋል፡፡ የአባት ምሳሌ በህይወታቸው እንዳይጎድል አንዳንድ ጊዜ እየመጣችሁ የአባትነትን ሚና ብትጫወቱ ፣ ብትመክሩዋቸው ፣ አብራችኋቸው ብትጫወቱ ብታበረታቱዋቸው ፣ ሲያጠፉ ብትቆጡዋቸው በልጆቹ ህይወት የሚጎድላቸውን የአባት ድርሻ ማሟላት ትችላላችሁ አሉን፡፡
እውነት ነው እግዚአብሄር ልጅ እንዲወለድ የፈለገው በአባትና በእናት በቤተሰብ መካከል ነው፡፡ የእግዚአብሄርን መልክ ሙሉ ለሙሉ የሚገልፀው አባትና እናት ናቸው፡፡ ስለዚህ ነው እግዚአብሄር ሰውን በመልኩ ወንድና ሴት አድርጎ የፈጠረው፡፡ ሴት የእግዚአብሄርን እንክብካቤ ፣ ልስላሴ ፣ ምህረት መልክ እንድታሳይ ወንድ ደግሞ የእግዚአብሄርን መሪነት ፣ ጥንካሬ ፣ ቁጣ ፣ እርማት መልክ እንዲያሳይ ነው፡፡
እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ዘፍጥረት 1፡27
ስለዚህ በአካባቢያችን እንመልከት የአባት ምሳሌ የምንሆንላቸውን ልጆች አይተን እናገልግል፡፡ የልጅ እድገት የአባትና የእናት ምሳሌ ግብአት ውጤት ነው፡፡ ከልጅ ጋር የምናወራው ወሬ እንኳን እንደአባት የምንጫወተው ሚና ለልጅ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ በሳምንት የአንድ ሰአት የአባትነት ምሳሌ ለልጅ ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ እስተዋኦ ያደርጋል፡፡  
ከስጋ ልጆቻቸው አልፈው ለሌሎች ልጆች የአባትነትን ሚና የሚጫወቱ ሁሉ እግዚአብሄር ይባርካቸው እንላለን!
መልካም የአባቶች ቀን !
ስለዚህ ለልጆች አባቶች እንሁን! 
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ወላጅ #ፍቅር #አባት #እርማት #ጥንካሬ #አባትነት #ተግሳፅ  #መሪ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ 

No comments:

Post a Comment