አምላኬም
እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4፡19
እንዳላችሁ
ንግድ ብዛት፣ እንዳላችሁ የባንክ ሂሳብ ፣ እንዳላችሁ የቤተሰብ ውርስ ፣ እንዳላችሁ ንግድ ትርፋማነት ፣ እንዳላችሁ የደሞዝ መጠን
፣ እንዳላችሁ የሃብት ልክ ይሞላባችኋል አላለም ቃሉ፡፡ የሚሞላብን እንደባለጠግነቱ መጠን ነው፡፡
ለምኑ
ፈልጉ አንኳኩ፡፡ ለምኑ ሲል ለምኑ ነው፡፡ ለመለመን ግን ኪሳችንን እዩ አላለም፡፡ ለመለመን የባንክ ሂሳባችሁን እዩ አላለም፡፡
ለመለመን የቤተሰባችሁን ሃብት እዩ አላለም፡፡ ለመለመን የደሞዛችሁን ልክ እዩ አላለም፡፡ ለመለመን የምናየው የባለጠግነቱን መጠን
ብቻ ነው፡፡
እንዳላችሁ
ንግድ ብዛት፣ እንዳላችሁ ንግድ ትርፋማነት ፣ እንዳላችሁ የባንክ ሂሳብ ፣ እንዳላችሁ የቤተሰብ ውርስ ፣ እንዳላችሁ የደሞዝ መጠን
፣ እንዳላችሁ የሃብት ልክ ለምኑ አላለም፡፡
ለምኑ፥
ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? ማቴዎስ 7፡7-11
ለሚጠሩት ደሞዝተኛ ሰራተኞች ፣ ለሚጠሩት ባለሃብቶች
፣ ለሚጠሩት ነጋዴዎች ፣ ለሚጠሩት ባለጠጎች ወይም ለሚጠሩት የባንክ ሂሳብ ባለቤቶች አላለም፡፡ ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ ነው፡፡ ባለጠግነቱ
ከእርሱ ከሚጠራው እንጂ ከእነርሱ ከሚጠሩት አይደለም፡፡ ለምነው ሲቀበሉ ጠርተውት ሲያባለፅጋቸው ብቻ ነው የሚበለፅጉት፡፡
በአይሁዳዊና
በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ ሮሜ 10፡12
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #መፀለይ #መለመን #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment