በፀሎት
ውስጥ የተጠራቀመ አጅግ ታላቅ ሃይል አለ፡፡ ስለፀሎት ያለን መፅሃፍ ቅዱሳዊ መረዳት በፀሎት ህይወታችን ፍሬያማ እንድንሆን ያደርጋል፡፡
ፍሬያማ ፀሎትን ከማየታችን በፊት ፍሬያማ ያልሆነን ፀሎት እስኪ እንመልከት፡፡
የጻድቅ
ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ያዕቆብ 5፡16
ፍሬያማ
ያልሆነ ፀሎት ንግግር ብቻ ነው፡፡
ፀሎት
ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር ነው፡፡ ፀሎት እግዚአብሄርን መስማትና ለእግዚአብሄር መናገር ነው፡፡ ሲጀመር እስኪጨረስ ለእግዚአብሄር
መናገር ጸሎት አይደለም፡፡ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን ስለማናውቅ ሃሳባችንን ለእግዚአብሄር መናገር ብቻ ንግግር እንጂ ፀሎት
አይደለም ፡፡
መክብብ
5፡2 ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ ለመስማት መቅረብ ከሰነፎች መሥዋዕት ይበልጣልና እነርሱም ክፉ እንዲያደርጉ አያውቁምና። እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኵል ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን።
ፍሬያማ
ያልሆነ ፀሎት የፈሪ ዱላ ነው፡፡
ፀሎት
የፈሪ ዱላ አይደለም፡፡ ፀሎት እግዚአብሄርን ከእንቅልፉ የምንቀሰቅስበት መጥሪያ ጩኸት አይደለም፡፡ ፀሎት ስለህይወታችን ለእግዚአብሄር
ካልነገርነው በስተቀር አያውቅም ብለን ለማሳወቅ የምንጥርበት ጥረት አይደለም፡፡ ፀሎት እግዚአብሄር የሚያስፈልገንን ስለማያውቅ የምናሳውቅበት
ማስታወቂያ አይደለም፡፡ ፀሎት እግዚአብሄር የማያውቀውን ነገር በመንገር የምናስደንቅበት መንገድ አይደለም፡፡
ስለዚህ
አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። ማቴዎስ 6፡8
ፍሬያማ
ያልሆነ ፀሎት እግዚአብሄርን ማስረጃ ነው፡፡
እግዚአብሄር
ከእኛ ፀሎት መረጃን ሰብስቦና ተረድቶ የህይወት እቅዳችንን የሚሰራበት መንገድ አይደለም፡፡ የህይወት እቅዳችን ቀድሞውንም በእርሱ
ዘንድ አለ፡፡
ለእናንተ
የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርሚያስ 29፡11
ፀሎት
በእረፍት እግዚአብሄርን መስማትና ለእግዚአብሄር መናገር ነው፡፡ ፀሎት
ከአባታችን እግዚአብሄር ጋር የአባትና የልጅ ህብረት የምናደርግበት መንገድ ነው፡፡ ፀሎት ከእግዚአብሄር ጋር ቁጭ የምንልበት መንገድ
ነው፡፡ ፀሎት እግዚአብሄር ከእኛ ምን እንደሚፈልግ የምንጠይቅበት መንገድ ነው፡፡ ጸሎት ምን ላድርግልህ የምንልበት መንገድ ነው፡፡
ፀሎት ምኔን ልስጥህ ብለን የምንጠይቅበት መንገድ ነው፡፡ ፀሎት እግዚአብሄርን ለመስማት ፣ ለመታዘዝና ለማገልገል በፊቱ የምንቀመጥበት
መንገድ ነው፡፡
ፀሎት
እንደ አስተናጋጅ ሁለት እጃችንን ወደኋላ አጣምረን እግዚአብሄር ከእኛ ምን እንደሚፈልግ የምንጠይቅበትና የምንሰማበት የአምልኮና
የህብረት ጊዜ ነው፡፡
እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ። በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ አለ። ሐዋርያት 13፡2
የእግዚአብሄር
መንፈስ ስለእኛ ወይም ስለሌላው እንዴት እንደምንፀልይ የሚመራን በፊቱ በእረፍት ስንሆን ነው፡፡ እንዴት መፀለይ እንደሚገባን መንፈስ
ሲመራን ፀሎታችን አላማውን ይመታል፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ቆይተን በምሪት የምንፀልየው ፀሎት ግቡን ይመታል፡፡ በእግዚአብሄር መንፈስ
ተደግፈን የምንፀልየው ፀሎት ጊዜ ሳይወስድ ዝም ብሎ እንደማይተኩስ ጠብቆ አነጣጥሮ አላማውን እንደሚመታ ተኳሽ በፀሎት ህይወታችን
ፍሬያማ ያደርገናል፡፡
እንዲሁም
ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤
ሮሜ 8፡26
No comments:
Post a Comment