ስጡ
ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል። ሉቃስ 6፡38
ሰው
መስጠት ማካፈል ይፈልጋል፡፡ ማንም ሰው መስጠትና ማካፈል ትክክል አንደሆነ ያውቃል፡፡ መስጠትና ማካለፈል መልካም ነገር እንደሆነ
የማይረዳ ሰው የለም፡፡ ሁሉም ሰው ስለመስጠት አስፈለካጊነት ያውቃል፡፡
ሰው
ግን እንዳይሰጥ የሚያደርገው ምንድነው? ሰው ታዲያ እንዳይሰጥ የሚያስፈራራው ምንድነው? ብለን ስንጠይቅ ይህን የሰውን ሁሉ አለም
አቀፋዊ ጥያቄ እንደሆነ እንረዳለን፡፡
ይህ
ሰው እንዳይሰጥ የሚያደርገው ጥያቄ የሰው ሁሉ ሃቀኛ ጥያቄ ነው፡፡ ሰው ለመስጠትና ለማካፈል ይህ እውነተኛ ጥያቄ በትክክል ሊመለስለት
ያስፈልገዋል፡፡ ይህን ጥያቄ ለሰው በሚገባ ሳይመለስለት ሰውን ስጥ ማለት አግባብ አይደለም፡፡
ግን
ሰው እንዳይሰጥ የሚያግደው ይህ ጥያቄ ምንድነው፡፡ ሰው ሊሰጥ ካለ በኋላ እንኳን እጁን እንዲመልሰው የሚያደርገው ጥያቄ ምን አይነት
ጥያቄ ነው?
ይህን
ጥያቄ ማንም ቢጠይቀው ማንም ሊኮንነው የማይገባው ሃቀኛ ጥያቄ ነው፡፡ ሰጥቼ እኔስ ባጣ የሚለው ጥያቄ በትክክል ሊመለስለት የሚገባው
እውነተኛ ጥያቄ ነው፡፡ ከሰጠሁ በኋላ እኔስ ቢጎድልብኝ የሚለው ጥያቄ አለም አቀፋዊ መለስ የሚገባው አለምአቀፋዊ ጥያቄ ነው፡፡
ስለዚህ
ነው ኢየሱስ ስጡ ብሎ ከተናገረ በኋላ ሰጥቼ ቢጎድልብኝስ የሚለውን የሰውን ጥያቄ መልሰ ሲሰጥ ይሰጣችሁማል ያለው፡፡
ስትሰጡ
ይሰጣችኋል፡፡ እንዲያውም አለ መስጠት ማቀበል ብቻ አይደለም፡፡ መስጠት ማስተላለፍ ብቻ አይደለም፡፡ መስጠት መዝራት ነው መስጠት
ማበርከት ነው፡፡ ስትሰጡ የሰጣችሁት ብቻ ሳይሆን በመልካም መስፈሪያ ተባዝቶ ይሰጣችኋል፡፡
እንዲያውም
መስጠት የሰጣችኋት ብቻ ተልክቶ ተመልሶ የምትሰጣችሁ አይደለም፡፡ ተመልሶ የሚሰጣችሁ የሰጣችሁት ብቻ ሳይሆን የተነቀነቀ የተጨቆነ
መስፈሪያ ይሰጣችኋል፡፡
ስጡ
ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ
ይሰጣችኋል። ሉቃስ 6፡38
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #መስጠት #ማካፈል #መባረክ #ስጡ #ምፅዋት #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #መዝራት #ከልቡ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #ድሃ #መፅሃፍቅዱስ #በደስታ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment