Popular Posts

Follow by Email

Thursday, June 8, 2017

ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ

ባለጠግነት ማለት በሚያስፈልገን ጊዜ የሚያስፈልገንን ነገር ማግኘት ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት ማለት እግዚአብሄር በምድር ላይ የሰጠንን ስራ ሰርተን ለማለፍ የሚያስፈልግንን አቅርቦት ሁሉ ማግኘት ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት ማለት ለእግዚአብሄር በሙላት ለመታዘዝ የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ አለማጣት ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት ማለት ጌታን በነገር ሁሉ መከተል እንድንችል አቅም ማግኘት ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት ማለት ከባለጠጋ አምላከ ጋር ያለ መልካም ግንኙነት ማለት ነው፡፡ ባለጠግነት ማለት ለጥሪያችን የሚያስፈልገንን ነገር አለማጣት ማለት ነው፡፡  
ባለጠግነት ማለት በእግዚአብሄር ዙፋን ቀርቦ ጉዳይን ማስፈፀም ማለት ነው፡፡ 
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ። ዕብራውያን 4፡16
ባለጠግነት ማለት የሚያስፈልገንን ሁሉ የሚጨምርልን የእግዚአብሄር ልጅ መሆን ማለት ነው ፡፡
ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል። ማቴዎስ 6፡32-33
ባለጠግነት ሁሉን ቻይ የሆነውን መታመንና መጥራት ነው፡፡
በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ ሮሜ 10፡12
ባለጠግነት ታላቅና ሃይለኛን ነገር ወደሚያደርገው መጮኽ ነው፡፡
ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ። ኤርምያስ 33፡3
ባለጠግነት ማለት ባለጠጋው የእግዚአብሄር ከእኛ ጋር መኖር ማለት ነው፡፡
እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴዎስ 28፡19-20
ባለጠግነት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? ወዳለው መለመን ነው፡፡
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? ማቴዎስ 7፡7-11
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #መፀለይ #መለመን #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment