ሁሉ
ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። ሮሜ 11፡36
ሁሉ
ከእርሱ
መልካምነት
ሁሉ ከእርሱ ነው፡፡ እኛም ከእርሱ ነን፡፡ የሚያቀርበው እርሱ ነው፡፡ መልካንም ነገር ለማድረግ የሚያስፈልገውን መነሳሳት እንኳን
የሚሰጠን እርሱ ነው፡፡ ድፍረትን የሚሰጠን ራሱ ነው፡፡ የሚያበረታን እርሱ ነው፡፡ ሁሉ ከእረሱ ነው፡፡
ሁሉ
በእርሱ ነው
ከእግዚአብሄር
ጋር አብረን የምንሰራ ነን፡፡ እርሱ ሲሰራ እንተባበረዋለን፡፡ እርሱ እየሰራ ነው፡፡ በእድል የሆነ ነገር የለም፡፡ ሁሉንም የነደፈው
እርሱ ነው፡፡ የሚጀምረውና የሚመራንና እርሱ ነው፡፡ እርሱ የሚሰራበትን ፈልገን እንተባበረዋለን፡፡ በእኛ ሃይል ለእግዚአብሄር አንኖርም
እግዚአብሄርንም በራሳችን ሃይል አናገለግልም፡፡ ሁሉ በእርሱ ነው፡፡
የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ
ነንና። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡9
ሁሉ ለእርሱ ነው
ሁሉንም እንዴት ለራሱ ክብርና ለእኛ ጥቅም እንደሚለውጠው ያውቃል፡፡ ሁሉ ለእርሱ
ክብር ነው፡፡ እግዚአብሄርን ማንም መጠቀሚያ ሊያደርገው አይችልም፡፡ እንዴት የሁሉንም ነገር መጨረሻ ለራሱ አላማ እንደሚለውጠው
ያውቃል፡፡ ክብሩንም ሁሉ መውሰድ ያለበት እግዚአብሄር ነው፡፡
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
ሮሜ 8፡28
ሁሉ
ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን። ሮሜ 11፡36
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#በእርሱ #ለእርሱ #ከእርሱ #ክብር #አላማ
#ኢየሱስ #ክርስቶስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ምህረት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment