ኢየሱስ
በዘር ስለሚመሰለው የእግዚአብሄር ቃል በምሳሌ ያስተምር ነበር፡፡ የዘርን ስኬት የሚወስነው የሚዘራበት የሰው ልብ እንደሆነ በምሳሌ
ያስረዳቸዋል፡፡
በምሳሌም
ብዙ ነገራቸው እንዲህም አላቸው፦ እነሆ፥ ዘሪ ሊዘራ ወጣ። ማቴዎስ 13:3
ሌላውም
በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው። ማቴዎስ 13:7
ሌላውም
በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾሁም አብሮ በቀለና አነቀው። ሉቃስ 8፡7
በእሾህ
መካከል የተዘራውም ይህ ቃሉን የሚሰማ ነው፥ የዚህም ዓለም አሳብና የባለጠግነት መታለል ቃሉን ያንቃል፥ የማያፈራም ይሆናል። ማቴዎስ 13:22
በእሾህ
መካከልም የወደቀ እነዚህ የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፥ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም። ሉቃስ 8፡14
የምንሰማውም የእግዚአብሄር ቃል ሃያል ሆኖ ሳለ
በህይወታችን እንዳይሰራ የሚያግደው አስቀድመን ልባችንን የሰጠንለት ነገር ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ ዕብራውያን 4፡12
አስቀድሞ ህይወታችንን የያዘው ነገር የምንሰማው
ቃል ሙሉ ፍሬ እንዳያፈራ ያንቀዋል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ለማደግና ለማፍራት በቂ እድል እንዳያገኝ ያስረዋል፡፡
የእግዚአብሄር ቃል ስፍራን አግኝቶ ሙሉ ፍሬ እንዳያፈራ
የሚገዳደረው አስቀድመን ልባችንን የሰጠንለት የኑሮ ጭንቀትና የባለጠግነት ምኞት ነው፡፡
ለኑሮ ጭንቀት ራሳችንን በሰጠን መጠን የእግዚአብሄር
ቃል በእኛ ላይ ሃይል እንዳይኖረው እናግደዋለን፡፡ ለባለጠግነት ማታለል ራሳችንን ከሰጠን የእግዚአብሄር ቃል በህይወታችን እንዳይሰራ
እንበርዘዋለን፡፡ የባለጠግነት ምኞት በህይወታችን ስፍራን ካገኘ የእግዚአብሄር ቃል ሙሉ ፍሬ እንዳያፈራ ያግደዋል፡፡
ፀሎት፡ እግዚአብሄር አባቴ ሆይ ይህንን ቃል እንድሰማ
ስለላክልፅ አመሰግንሃለሁ፡፡ ቃልህን ሰምቻለሁ፡፡ የኑሮ ጭንቀት ቃልህ በህይወቴ እንደሚገባው አንዳይሰራ እንደሚያግደው ከቃልህ ተረድቻለሁ፡፡
እግዚአብሄር ሆይ አንተን እታዘዛለሁ፡፡ በህይወቴ ለጭንቀት ፊት አልሰጥም፡፡ ፀጋህ ስለሚረዳኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ አሜን
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ጭንቀት #የኑሮሃሳብ #ብልፅግና
#የባለግነትምቾት #ዘር #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment