የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ ማቴዎስ 6፡11
ለአብዛኞቻችን
መሰረታዊ ፍላጎት ዋና የህይወት ጥያቄ አይመሰለንም፡፡ ነገር ግን ዋናው የህይወት ጥያቄ የእለት እንጀራ ነው፡፡ የእለት እንጀራ
ለኑሮ የሚያስፈልገን መሰረታዊ ፍላጎትን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡
በህይወት
ስለብዙ "ትልልቅ" ነገሮች ጌታን ማመን ያለብን ይመስለናል፡፡ ሰው ለመሰረታዊ ፍላጎት እግዚአብሄርን ካመነ አረፈ
ማለት ነው፡፡ ምክኒያቱም በህይወት የሚያስፈልገው ዋና ነገር መሰረታዊ ፍላጎትን አማልቶ ጌታን መከተል ነው፡፡
የመኖር
አላማችን ጌታን መከተል ፣ ለጌታ መኖርና ኢየሱስን በህይወታችን ማክበር ነው፡፡ የምንኖረው ለመኖር ብቻ አይደለም፡፡ የምንኖረው
ኢየሱስን በመምሰል ስለ ኢየሱስ አዳኝነትና ጌትነት በምድር ላይ ለመመስከር ነው፡፡
ስለ
ኢየሱስ አዳኝነትና ጌትነት በምድር ላይ ለመመስከር የሚያስፈልገን መሰረታዊ ፍላጎታችን መሟላቱና ነው፡፡
ብዙ
ሰው ስለብዙ ነገር ታላቅ እምነት እንዲኖረው ይፈልጋል፡፡ ሰው ኢየሱስ ስለ እርሱ ሃጢያት በመስቀል ላይ እንደሞተ ከማመን ቀጥሎ
የመጀመሪያውና መሰረታዊው እምነት ስለ እለት እንጀራው ወይም ስለመሰረታዊ ፍላጎቱ ጌታን ማመን ነው፡፡
ስው
ስለ መሰረታዊ ፍላጎቱ ጌታን ካላመነ ስለምንም ሌላ ነገር አምናለሁ ሊል ይዋሻል፡፡ ሰው ስለመሰረታዊው ፍላጎቱ ካላመነ ስለ ትልልቅ
ነገር ጌታን አምናለሁ ቢል ምንም አይጠቅመውም፡፡
ሰው
ስለ መሰረታዊ ፍላጎቱ ስለሚበላው ፣ የቤት ኪራይ ስለሚከፍለው ፣ ስለ ልጆቹ ትምህርት ቤት ፣ ስለ መኪናው ነዳጅ ጌታን ካመነ እግዚአብሄርን
በነፃነት ማገልገል ይችላል፡፡ የኑሮ ጭንቀት ፊት ከሰጠነው ማናችንንም በቁማችን ሊውጠን ስለሚችል ሰው ስለመሰረታዊ ፍላጎቱ ጌታን
ካላመነ ጌታን ለማገልገል ነፃነት ሊኖረው አይችልም፡፡
ሰው
ብዙ አላስፈላጊ እርምጃ ሲወስድ የሚየታየው ስለመሰረታዊ ፍላጎት ጌታን ባለማመኑ ነው፡፡ ሰው የሚዋሸው ፣ የሚያጭበረብረው ፣ ሌላውን
የሚጠላው ስለመሰረታዊ ፍላጎት ጌታን ስለማያምን ነው፡፡
ስለመሰረታዊ
ፍሎጎቱ ጌታን ያመነ ሰው ጌታ የእለት እንጀራውን በእለቱ እንደሚሰጠው አጥብቆ የተረዳ ሰው ፀጥና ዝግ ብሎ በመኖር ጌታን ሲያሳይ
ለብዙዎች ምሳሌ ሊሆንና በሚቀናበት የክርስትና ህይወት ጌታን በምድር ቆይታው ሲያስከብ እናያለን፡፡
የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ ማቴዎስ 6፡11
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ጭንቀት #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለግነትምቾት #ዘር
#መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ
#መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment