Popular Posts

Friday, January 12, 2024

ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ! ክፍል 6

 


ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ 1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 729

ጋብቻ ክቡር ነው፡፡ ጋብቻ እግዚአብሄር አላማ የምንፈፅምበት ወርቅማ እድል ነው፡፡ ይህ ግን የሚሆነው  ባልም ሆነ ሚስት በየግላቸው እኔ ለትዳሩ ምን አድርጋለሁ? ምን የምሰጠው ነገር አለኝ? ምን አበረክታለሁ? በሚለው ሃላፊነታቸው ላይ ሲያተኩሩ ብቻ ነው፡፡

ትዳር የሚሰምረው የትዳር አጋሩ ከደስታ እና ከሙላት ሲያገባ እና ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ሰው ስለጎደለው የሚያገባ ከሆነ ትዳር በዋነኝነት የሰውን ጉድለት ለማሟላት ያልታቀደ ስለሆነ ይሰናከላል፡፡ ሰው በትዳር የሚቆየው በዋነኝነት እንዳይጎድለው በምስኪን እኔ አስተሳሰብ ከሆነ እግዚአብሄር በትዳር ውስጥ ያስቀመጠውን በረከት ሳያገኝ ይቀራል፡፡

ባል ሚስቱን ለመባረክ እና የተባረከች እና የሚቀናባት ሴት በማድረግ ላይ ሲያተኩር ትዳሩ ይሰምራል፡፡ ሴትም ባልዋን እንዲወጣ እንዲያሸንፍ በመርዳት ላይ ስታተኩር እና ስትደግፈው ትዳሩ እግዚአብሄር ያቀደለትን አላማ ይፈፅማል፡፡  

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ያገባ #ያላገባ #አላፊ #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ሚስት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ባል #እምነት #ወንድ #ፍቅር #ትዳር #ሰላም #ሴት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ


No comments:

Post a Comment