ለሰው የሚያስፈልገውን ማንኛውም ነገር ሁሉ በአምስት
ቀን ውስጥ ከሰራ በኋላ ሰውን እግዚአብሔር የፈጠረው በስድስተኛ ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ከፈጠረ በኋላ በሰባተኛው ቀን ከሰው
ጋር አረፈ፡፡ ሰው በስድስተኛ ቀን የተፈጠረው ከእግዚአብሔር ጋር በሰባተኛው ቀን እንዲያርፍ ነው፡፡
ሰው የተሰራው ለእረፍት ነው፡፡ ሰው ምንም ነገር
ቢሰራ እንኳን የተሰራው በእረፍት እንዲሰራ ነው፡፡ እረፍት ማለት አለመስራት ማለት አይደለም፡፡ እረፍት ማለት አለመባዘን ፣ አለመባከን
፣ አለመጨነቅ ፣ አለመታሰር ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ነው እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል የሃጢያታችንን
እዳ ሁሉ ከከፈልልን በኋላ እረፉ የሚለን፡፡
እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ማቴዎስ 11፡28-29
ከመስራት
በፊት ማረፍ ይቀድማል፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገው አርፈን በራሱ ምሪትና ሃይል ብቻ እንድንሰራ ነው፡፡ በራሳችን ሃይልና ጉልበትን እንድንፍጨረጨር አይፈልግም፡፡
ስለዚህ
ነው በመንፈሴ እንጂ በሃይልና በብርታት አይደለም የሚለው፡፡
መልሶም፦
ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡
ዘካርያስ 4፡6
ሰው
የሚያርፈው ተጨማሪ ገንዘብ ሲኖረው አይደለም፡፡ ሰው የሚያርፈው ሰው የሚያርፈው እግዚአብሄርን ሲያውቅ ነው፡፡ ሰው የሚርፈው እግዚአብሄርን
ሲያይ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው በእግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡
ዕረፉ፥
እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፤ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። መዝሙር 46፡10
ሰው
የሚያርፈው በራሱ ከመሮጥ ሲመለስ ነው፡፡ ሰው የማያርፈው በራሱ ከመፍጨር ሲያርፍ ነው፡፡ ሰው የሚያርፈው በፀጥታ እግዚአብሄርን
ሲመለከት ነው፡፡ ሰው ሃያል የሚሆነው በእግዚአብሄር ሲያርፍ ነው፡፡ ሰው የሚበረታው በእግዚአብሄር ሲታመን ነው፡፡
የእስራኤል
ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፣ በፀጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፡፡ ኢሳያስ 30፡15
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት
#መደገፍ #ሰንበት
#በመንፈሴ #በሃይል #በብርታት #ፀጥታ #መመለስ #ማረፍ
#ፅድቁን #ኢየሱስ
#ክርስቶስ #ጌታ
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ
#መንፈስቅዱስ #መታመን
#ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment