እንደ
ሌሎቹ ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች እንደ ኬፋም፥ እኅት ሚስታችንን ይዘን ልንዞር መብት የለንምን? 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡5
የጋብቻ ግንኙነት የሚጀመረው በእህትነትና በወንድምነት
ነው፡፡ ወንድ የሚያጋባው በጌታ እህቱ የሆነችውን ሴት ነው፡፡ ሴት የምታገባው በጌታ ወንድሟ የሆነውን ወንድ ነው፡፡ የትዳር መሰረቱ
በጌታ የእህትነትና የወንድምነት ዝምድና ነው፡፡
ትዳር ከትዳር የፍቅር ግንኙነት አይጀምርም፡፡
ትዳር የሚጀምረው ከወንድምነት ፍቅር ነው፡፡ ትዳር የሚጀምረው ከእህትነት ፍቅር ነው፡፡ የትዳር የፍቅር ግንኙነት የሚጀመረው ከእህትነት
የፍቅርና የርህራሔ ግንኘነት ነው፡፡ የትዳር የፍቅር ግንኙነት የሚጀምረው ከወንድምነት የፍቅርና የርህራሔ ግንኙነት ነው፡፡ ትዳር
የሚጀምረው ከቤተሰብነት የፍቅር ግንኙነት ነው፡፡
የክርስትያናዊ ጋብቻ ግንኙነት መሰረቱ የእህትነትና
የወንድምነት ግንኙነት ነው፡፡ የጋብቻ ግንኙነት መሰረቱ የቤተሰብነት ግንኙነት ነው፡፡ የትዳር የርህራሔና የፍቅር ግንኙነት የሚጀምረው
ከወንድምነትና ከእህትነት የርህራሄና የፍቅር ግንኙነት ነው፡፡
ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሰረች ናት፤ ባልዋ
ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት። 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡39
ባልና ሚስት ከመሆናቸው በፊት እህትነትና ወንድም
መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ የባልና የሚስት ፍቅር ከማሳየታቸው በፊት የወንድምና የእህት ፍቅር ሊያሳዩ ይገባቸዋል፡፡ እንዲያውም ለባልና
ለሚስትነት ፍቅር መሰረት የሚሆነው የእህትነትና የወንድምነት ፍቅር ነው፡፡ ለባልነትና ለሚስትነት ዝቅተኛው መመዘኛ የእህትነትና
የወንድምነት ፍቅር ነው፡፡ የእህትነትና የወንድምነት ፍቅር የሌላቸው የባልነትና የሚስትነት ፍቅር ይኖራቸዋል ብሎ መጠበቅ አይቻልም፡፡ ከባልነቱ በፊት ወንድምነቱ
ይቀድማል ከሚስትነትዋ በፊት እህትነትዋ ይቀድማል፡፡ ባልና ሚስትነቱ ወንድምና እህትነቱን በፍፁም አይሽረውም፡፡
በትዳር የእህትነትና የወንድምነት ፍቅር እየጨመረ
ሊሄድ ይገባዋል እንጂ ሊቀንስ አይገባውም፡፡ ባልና ሚስት በሆኑም ጊዜ ወንድምና እህትነቱ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ በትዳር የወንድምነትና
የእህትነት ፍቅር እየጨመረ ሊሄድ ይገባዋል እንጂ በባልነትና በሚስትነት ፍቅር ሊተካ አይገባውም፡፡ በትዳር ባለቤትህ እህትህ ነች፡፡
በትዳር ባለቤትሽ ወንድምሽ ነው፡፡ በትዳርም የእህትነትና የወንድምነት ፍቅር ከባልነትና ከሚስትነት
ፍቅር ይቀድማል፡፡ የወንድምና እህትነቱ ፍቅር ለባልና ለሚስትነቱ
ፍቅር ጉልበት ይሰጠዋል፡፡
የእህትነትና የወንድምነት ፍቅር ከትዳር ፍቅር መቅደሙ በቻ ሳይሆን የእህትነትና
የወንድምነት ፍቅር ለትዳር መሰረት ነው፡፡ ከትዳርም በኋላ እንዲሁ በሰማይ የሚዘልቀው የወንድምነትና የእህትነት ግንኙነት እንጂ የባልነትና የሚስትነት ግንኙነት አይደለም፡፡
በትንሣኤስ
እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም። ማቴዎስ 22፡30
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ፍቅር #ጋብቻ #ትዳር #ባል #ሚስት #አንድስጋ #እውነት #እህትነት #ወንድምነት #መውደድ #ወንጌል #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment