Popular Posts

Tuesday, August 15, 2017

የአጋርነት ሃይል - በንግድ

የህይወት ስጦታ ሁሉ በአንድ ሰው ውስጥ የለም፡፡ በህይወት ስኬታማ ለመሆን እያንዳንዳችን ሌሎች ያስፈልጉናል፡፡ ስኬታማ ለመሆን በህይወታችን እኛ የሌለን ስጦታ ያላቸው ሰዎች ያስፈልጉናል፡፡ የአንድን ሰው ህይወት የሚሰራው የሰዎች አስተዋፅኦ ነው፡፡ በህይወት ለመከናወን በአንዳንድ የህይወት ክፍላችን ከእኛ የተሻሉ ሰዎች ያስፈልጉናል፡፡ ላላው ከእኛ እንደሚሻል ካላወቅን በሰዎች የተሻለ ስጦታ መጠቀም ያቅተናል፡፡ ትኩረታችን በራሳችን ስጦታና ችሎታ ላይ ብቻ ከሆነ  የሌሎችን ስጦታ አስተዋፅኦ በህይወታችን እንገድላለን፡፡
ለእኛ ተራራ የሚሆንብንን ነገር በቀላሉ የሚሰራው ሌላ ሰው አለ፡፡ ለእኛ ጭንቅ የሚሆንብን ነገር ለሌላው እንደ ጨዋታ ነው፡፡ የስጦታችን መለያየት ልዩ ያደርገናል እንጂ እኛን ታናሽ ሌላውን ታላቅ አያደርገውም፡፡ በሌላው ስጦታና ክህሎት ለመጠቀም በተወሰነ የህይወት ክፍል ሌላው ከእኛ እንደሚሻል በትህትና መቁጠር ይጠይቃል፡፡
ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ ፊልጵስዩስ 2፡3
ለህይወት ስኬት አጋርነት ወሳኝ ነው፡፡
የንግዱን አለም ብንመለከት በአለም ላይ በንግድ ታላላቅ ጥርመሳዎች የመጡት በንግድ አጋርነት አማካኝነት ነው፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ ነጋዴ ደንበኛን የማሳመንና ወጥቶ ምርቱን የመሸጥ ልዩ ችሎታ አለው፡፡ አንዳንዱ ነጋዴ ደግሞ ንግዱን ማስተዳደር የሚገባውንና የሚወጣውን እቃ መከታተል  እንዱሁም የተሸጡትን እቃዎች ተከታትሎ ገንዘቡን በመቀበል በመሳሰሉት የአስተዳደር ስራ የተካነ አለ፡፡ ስለዚህ በመሸጥ የተካነው ነጋዴና በማስተዳደር የተከናው ነጋዴ በአጋርነት ቢሰሩ ሁለቱ በተናጥል ከሚሰሩት የተሻለ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ አንድ ንድግ በአንድ ሰው ክህሎት ላይ ብቻ ካልተደገፈና አጋሮቹ ሁሉ በጠንካራ ጎናቸውና በየክህሎታቸው ለድርጅቱ ጠንክረው ከሰሩ ድርጅቱ የማያድግበት ምክኒያት አይኖርም፡፡
ድርጅቱ ሲያድግ እምዲሁ አንዱ ለሌላው አስተዋፅኦ እውቅና ካልሰጠ እና ክብሩን ሁሉ ጨቅልሎ ኪሱ ከከተተ አጋርነቱ ሊቀጥል ብሎም በአጋርነቱን የሚገኘው ጥቅም ሊቀጥል አይችልም፡፡ የድርጅቱ ማደግና መስፋት እንጂ ክብሩን ማን ይወስደዋል የሚለው ትልቅ ጥያቄ ካልሆነ በአጋርነት ድርጅት ያድጋል፡፡ በድርጅት እድገት ሲመጣ በአጋሮቹ ሁሉ ምክኒያት እንደመጣ እውቅና መስጠት ይጠይቃል፡፡  
አንዳንድ ጊዜ ግን በአጋርነት የመጣውን እድገት የእኛ ብቻ ለማድረግ ስንሞክርና በአጋርነት ሃይል የመጣውን ውጤት በእኛ ምክኒያት የመጣ ሲመስለን እንታለላለን፡፡ በአጋርነት የተለቀቀው ጥቅምን "ይህ አጋሬ ባይኖር ኖሮ ክንሩንና ጥቅሙ ሁሉ የኔ ይሆን ነበር" ብለን ካሰብን ነገር ይበላሻል፡፡ በአጋርነቱ ሁሉ ምክኒያት ጥቅሙ እንደመጣ ማስተዋል ነው፡፡ የመጣውን ውጤት ብቻ ሳይሆን በአጋርነቱ ላይ  የተደረገውን አስተዋፅኦ ብንመለከት አጋሬ ባይኖር ኖሮ ይህ ሁሉ የእኔ ይሆን ነበር ወደሚል አላግባብ ቁጭት ውስጥ አንገባም፡፡
ለተሻለ ጥቅም በአገፋርነት ለመስራት ራሳችንን ትሁት እናድርግ፡፡ በአጋርነት የመጣውን ድል የራሳችን ብቻ አናድርገው፡፡ እግዚአብሄር የሚባርከን አጋርነትን ሁሉ አይቶ ነው፡፡ በአጋርነት ያገኘነው ድል ብቻችንን ብንሆን ኖሮ የማናገኘው ድል ነው፡፡ ሚስት ስናገባ የሚለቀቅልን በረከት ሚስት ካላገባው ይጨምራል፡፡   
ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ይቀበላል። ምሳሌ 18፡22
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህብረት #አጋርነት #አብሮማደግ #የጋራ #ንግድ #ሚስት #የባለጠግነትማታለል #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለግነትምቾት #ዘር #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment