ሄኖክም
አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና። ዘፍጥረት 5፡24
ሄኖክ
ከእግዚአብሄር ጋር አኩል ተራመደ፡፡ ሄኖክ እግዚአብሄርን ጠበቀ፡፡ ሄኖክ እግዚአብሄርን ሰማ፡፡ ሄኖክ እግዚአብሄርን አልቀደመም፡፡
ሄኖክ ከእግዚአብሄር አልዘገየም፡፡ ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሄር ጋር አደረገ፡፡
ሄኖክ
በአካሄዱ ከእግዚአብሄር እኩል ወጣ ከእግዚአብሔር እኩል ገባ፡፡ ሄኖክ በአካሄዱ በእግዚአብሄር ኖረ፡፡
መኖሪያህ
የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ዘዳግም 33፡27
ሄኖክ
በአካሄዱ በእግዚአብሄር ውስጥ ተሸሸገ፡፡ ሄኖክ በአካሄዱ በእግዚአብሄር ተተገነ፡፡ ሄኖክ በአካሄዱ በእግዚአብሔር ተሰወረ፡፡
አቤቱ
ጕልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ። እግዚአብሔር ዓለቴ፥ አምባዬ፥ መድኃኒቴ፥ አምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ፥ መታመኛዬና የደኅንነቴ
ቀንድ መጠጊያዬም ነው። መዝሙር 18፡1-2
ሄኖክ
በአካሄዱ በእግዚአብሄር ውስጥ ተሰወረ፡፡
ሄኖክ
አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፡፡ ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሄር ጋር ስላደረገ ውድቀት አላገኘውም፡፡ ሄኖክ ከእግዚአብሄር
እኩል ስለተራመደ ሽንፈትን አልቀመሰም፡፡
ሄኖክም
አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና። ዘፍጥረት 5፡24
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ራእይ #እይታ #መጠበቅ #መተማመን #እምነት #መራመድ #መውጣት #መግባት #አልተገኘም
#እግዚአብሔር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አካሄድ #አሸናፊ #አማልክት #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሔርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment