ያዕቆብ
ሆይ፤ ለምን እንዲህ ትላለህ? እስራኤል ሆይ፤ ለምን እንዲህ ትናገራለህ? “መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች፤ ፍርዴም በአምላኬ
ቸል ተብላለች” ለምን ትላለህ? አታውቅምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፣ የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው። አይደክምም፤
አይታክትም፤ ማስተዋሉም በማንም አይመረመርም። ለደከመው ብርታት ይሰጣል፤ ለዛለው ጒልበት ይጨምራል። ወጣቶች እንኳ ይደክማሉ፤ ይታክታሉም፤
ጐበዛዝትም ተሰናክለው ይወድቃሉ። እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤
አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም። ኢሳይያስ 40፡27-31 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
በአለም
የሚያደክም ብዙ ነገር አለ፡፡
ጎበዝ
የተባለ ፣ ጠንካራ የተባለና ሃያል የተባለ ሰው በራሱ አይቆምም፡፡ ይወድቃል ብለን የማናስበው ሰው ወድቆ እናገኘዋለን፡፡ ማንም
ሰው ላለመውደቅ መተማመኛ የለውም፡፡
በተቃራኒው
ደግሞ እግዚአብሄርን የሚጠብቁ ሰዎች አይደክሙም፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የሚራመዱ ሰዎች በድካም አይሸነፉም፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር
የሚኖሩ ሰዎች ከድካም በላይ ናቸው፡፡ ሰው ሳይደክም እንደበረታ የሚኖረው እግዚአብሄርን ሲጠብቅ ብቻ ነው፡፡ ሰው ከድካም በላይ
የሚኖረው ከእግዚአብሄር ጋር ሲራመድ ብቻ ነው፡፡
ሰው
ሃይሉን የሚያድሰው እግዚአብሄርን ካልቀደመው ነው፡፡ ሰው ሃያል የሚሆነው በእግዚአብሄር ፍጥነት ለመኖር ራሱን ትሁት ካደረገ ነው፡፡
ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ከኖረ የእግዚአብሄር ሃይል በእርሱ ላይ ይሆናል፡፡ ሰው በራሱ ከሮጠ ይደክማል ይወድቃል፡፡
እግዚአብሄር
የሚያነሳበት ጥበብ አለው፡፡ አግዚአብሄር የሚያሻግርበት መንገድ አለው፡፡ እግዚአብሄር የሚክስበት መንገድ አለው፡፡ እውቀት በሌለን
ነገር በእግዚአብሄር ልንታመንና ልንደገፍ ይገባናል፡፡ የእግዚአብሄርን አሰራር ልንታገስ ይገባል፡፡ የእግዚአብሄርን ፍጥነት ልንጠብቅ
ይገባናል፡፡
ያዕቆብ
ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?
አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም።
ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ እግዚአብሔርን
በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም። ኢሳይያስ
40፡27-31
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ራእይ #እይታ #መጠበት #መተማመን #እምነት #ያድሳሉ #ይወጣሉ #አይደክሙም #አይታክቱም #እግዚአብሔር
#አማርኛ
#ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #አሸናፊ #አማልክት #የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሄርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment