አንድ
አሳ አጥማጅ ነበር ይባላል፡፡ ብቻውን ሲኖር በቀን አንድ አሳ ያጠምዳል ይጠብሳ ይበላል ይተኛል፡፡ ሰዎች ሚስት አግባ ብለው መከሩት፡፡
ሚስት ካገባ በኋላ በቀን ሁለት አሳ ማጥመድ ጀመረ፡፡ ልጅ ሲወልድ ሶስት አራት አምስት አሳዎች ያጠምድ ጀመረ፡፡ እንደዚህ እያለ
ሰባት ልጆች በመውለዱ ከሚስቱ ጋር የሚበቃውን በድምሩ ዘጠኝ አሳ ያጠምድ ጀመረ፡፡
ሳያገባ
ሲያጠምድ ከነበረው አንድ ብቻ አሳ ጋር ሲያስተያየው ዘጠኝ አሳ ብዙ ነው፡፡ እና ምን አለ ይባላል? ሚስቴና ልጆቼ ባይኖሩ ኖ ዘጠኙም
የእኔ ይሆኑ ነበር አለ ይባላል፡፡ ነገር ግን በውስጡ የተቀመጠው ዘጠኙ አሳዎች የመጡት ሚስት በማግባቱና ልጆች በመውለዱ መሆኑን
ዘንግቶት ነበር፡፡
የዚህ
አሳ አጥማጅ ታሪክና በመጨረሻ የተናገረው ንግግር ቢያስገርመንም እንደ አሳ አጥማጁ የሚያስቡ ብዙ ሰዎች እንዳሉ እንመለከታለን፡፡
እግዚአብሄር እንደ ቤተሰብ የባረካቸው በረከት የእነርሱ ብቻ አድርገው የሚያስቡ፡፡ እራሳቸውን ብቻ የተመረቁ ሰዎች አድርገው የሚያዩና
ሌላውን ግን ዝቅ አድርገው የሚመለከቱ ሰዎች አሉ፡፡
ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ይቀበላል። ምሳሌ 18፡22
መፅሃፍ
ሚስትን ያገኘ ከእግዚአብሄር ሞገስን ይቀበላል ይላል፡፡ ሰው ሚስት ሲያገባ በሚስቱ ስም የእግዚአብሄር አቅርቦት ይጨምራል፡፡ ሰው
ሚስት ሲያገባ ካላገባው ሰው ይልቅ እንደ ቤተሰብ ሞገሱ ይበዛል፡፡ ሰው ልጅ ሲወልድ እንዲሁ ለተጨማሪ በጀት ሞገሱ ይጨምራል፡፡
እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የራሱን በጀት ይዞ ነው ወደ ቤተሰቡ የሚመጣው፡፡
እግዚአብሄር
መጀመሪያ ስለሚስቱ ከዚያም ስለልጆቹ ብሎ የባረከውን በረከት ሁሉ ወደ ራሱ ስም የሚያዞር ፣ ሁሉም በእርሱ ቅልጥፍና ምክኒያት እንደመጣ
የሚቆጠር ሰው የተሳሳተ መረዳት ያለው ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር ቤተሰብን የሚባርከው ሁሉንም የቤተሰብ አባላት አስቦ ነው፡፡ እግዚአብሄር
አቅርቦቱ የሚጨምረው በቤተሰቡ ውስጥ ባሉት አጋሮች ብዛት ልክ ነው፡፡
አንድ
በቅርብ የማውቃት እህት ከመስራ ቤት ደሞዝ ሲጨመርላት ለቤት ሰራተኛዋ ደሞዝ ትጨምራለች፡፡
እግዚአብሄር
ስለንግድ ድርጅቱ አባላት የባረከውን በረከት ሁሉ ለመዋጥ የሚፈልግ ሰውና እግዚአብሄር ድርጅቱን የባረከው በድርጅቱ ስለሚሰሩት ሰዎች
ሁሉ ምክኒያት እንደሆነ የማያስብ ሰው የእግዚአብሄርን የበረከት መንገድ ያልተረዳ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሄር የምታገለግላቸውና የሚጠቅሙህን
ደንበኞች የሚልከው ስለድርጅቱ አጋር ባለቤቶችና በድርጅቱ ውስጥ ስለሚሰሩት ሰዎች ሁሉ ምክኒያት ነው፡፡ ድርጅቱ ሲያድርግ ሁሉም
አብሮ እንዲያድግ እንጂ አንድ ሰው ብቻ ተለይቶ እንደተመረቀ ሁሉንም ክብር ወደራስ ማድረግ የእግዚአብሄር አሰራር አይደለም፡፡ የድርጅቱ
ሰራተኞች ሁሉ እንደ አጋር ሰራተኛ እንጂ ባለቤቱን ሊጠቅሙ ብቻ እንደቀመጡ ያልታደሉ ሰዎች መቁጠር አግባብ አይደለም፡፡
ቤተክርስትያንም
ሆነ አገልግሎት ሲያድግ የእግዚአብሄር ሞገስ የመጣው በአገልጋዪችና በተጠቃዎቹ ሁሉ ፍላጎት ምክኒያት እንደሆነ ተረድቶ ሁሉንም ተጠቃሚ
የሚያደርግ ካልሆነ በረከቱ መሰረት አይኖረውም፡፡ አገልግሎቱን እንደ አጋርነት ካላየው አንድ ሰው ብቻውን እንደ ተመረቀ ሌሎች ለእርሱ
እንዲሰሩ እንደተፈጠሩ መቁጠር ሞኝነት ነው፡፡ ሁላችንም አብረን እንድናድግ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡ ስለ ህብረትና አጋርነት የመጣውን
የእድገትን ክብር ለብቻ ጠቅልሎ መውሰድ ስህተት ነው፡፡
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ህብረት #አጋርነት
#አብሮማደግ #የጋራ
#ሚስት #የባለጠግነትማታለል #የኑሮሃሳብ #የእለትእንጀራ #የባለግነትምቾት #ዘር #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment