የተጠራነው በእምነት ለመኖር ነው፡፡ ሁልጊዜ በእምነት
እንመላለስ፡፡
እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡6-7
የተጠራነው ለእግዚአብሔር ልጅነት ነው፡፡ የተጠራነው
የመለኮት ባህሪ ለመካፈል ነው፡፡
እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ ኤፌሶን 4፡1
የተጠራነው
በፍቅር ለመመላለስ ነው፡፡
እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ። ኤፌሶን 5፡1-2
የተጠራነው
በነገር ሁሉ ጌታን ደስ ለማሰኘት ለጌታ እንደሚገባ እንድንመላለስ ተጠርተናል፡፡
ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገሥ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ፥
በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን። ቆላስይስ 1፡12
በመንፈስ እንድንመላለስ ተጠርተናል፡፡
የእግዚአብሄር ቃል የመንፈስን ነገር በማሰብ በመንፈስ
መመላለስ፡፡
በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ። ገላትያ 5፡25
በውጭ
ባሉት ዘንድ በአግነባኑ እንድንመላለስ ተጠርተናል፡፡
ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ . . . እንዳዘዝናችሁም፥
በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን። 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡11-12
በየትኛውም ጊዜ ቢታይ እንደማያሳፍር በብርሃን
በታማኝነት ለመመላለስ ተጠርተናል፡፡
ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤ የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን
ልጆች ተመላለሱ፤ ኤፌሶን 5፡8-10
በአጠቃላይ ወደ መንግስቱና ወደ ክብሩ ለጠራን
ለእግዚአብሄር አንደሚገባ እንድንመላለስ ተጠርተናል፡፡
ወደ መንግሥቱ ወደ ክብሩም ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እየመከርንና እያጸናን እየመሰከርንላችሁም፥ አባት ለልጆቹ እንደሚሆን ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሆንን ታውቃላችሁና። 1ኛ ተሰሎንቄ 2፡11-12
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ራእይ
#እይታ #መጠበቅ
#መመላለስ #እምነት
#መራመድ #መውጣት
#መግባት #አልተገኘም
#እግዚአብሔር #አማርኛ
#ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #አካሄድ
#አሸናፊ #አማልክት
#የእግዚአብሄርእቅድ #የእግዚአብሔርፈቃድ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment