Popular Posts

Saturday, August 28, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 13

 

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 13
ለፈውስ እምነት ይጠይቃል፡፡ እኛ ብዙን ጊዜ ራሳችንን ዝቅ አድርገን እንደምናየው እግዚአብሄር አያየንም፡፡ ለፈውስ እምነት ይጠይቃል፡፡ 
እግዚአብሄር በኢየሱስ ክርስቶስ የሰራውን ለማየትና ለመጠቀም የእምነት እጅ ይጠይቃል፡፡ ፈውስን የምንቀበለው በእምነት ነው፡፡ 
ስለዚያም ነው ኢየሱስ ቃሉን ይሰብክ ነበር፡፡ ኢየሱስ በምድር አገልግሎቱ የእግዚአብሄርን ልብ ያሳይ ነበር፡፡ ኢየሱስ በምድር አገልግሎቱ እግዚአብሄርን ይተርከው ነበር፡፡ 
ፈውስን የሚያመጣው ለእኛ ያለውን የእግዚአብሄርን የፈውስ ፈቃድ መረዳት ስለሆነ በኢየሱስ የምድር አገልግሎት ዘመን ሰዎች ኢየሱስን ሊሰሙትና ሊፈወሱ ይመጡ ነበር፡፡ 
ከእነርሱም ጋር ወርዶ በተካከለ ስፍራ ቆመ፥ ከደቀ መዛሙርቱም ወገን ብዙ ሕዝብ ነበረ፥ ደግሞም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ከይሁዳ ሁሉ ከኢየሩሳሌምም ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ዳርም የመጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ሉቃስ 6፡17
ኢየሱስ ኢየሱስ ስለሆነ ብቻ ከቃሉ ውጭ ምንም ሊያደርግላቸው አይችልም ነበር፡፡ ፈውስ ያለው የእግዚአብሄርን ሃሳብ በመረዳት ውስጥ ስለሆነ በኢየሱስ አገልግሎት ሰዎች ኢየሱስን ሊሰሙትና ሊፈወሱ ይመጡ ነበር፡፡ 
ወሬው ግን አብዝቶ ወጣ፥ ብዙ ሕዝብም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ይሰበሰቡ ነበር፤ ሉቃስ 5፡15
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa 
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment