Popular Posts

Friday, August 13, 2021

ወደ ጸሎት አትቸኩል

 

የጸሎት ቃላትን ለመናገር መቸኮል ብዙም አይረዳም።

ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤ ለመስማት መቅረብ ከሰነፎች መሥዋዕት ይበልጣልና፤ እነርሱም ክፉ እንዲያደርጉ አያውቁምና። እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኵል፤ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን። መክብብ 5:1-2

ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ፈጥናችሁ በፀሎት ለመናገር አትጨነቁ።

በጸሎት ውስጥ በጣም አስፈላጊው ነገር ውጤትን የሚያመጣ ትክክለኛውን ነገር መናገር እንጂ አንድ ነገር ፈጥኖ በእግዚአብሄር ፊት መናገር አይደለም።

መልስ ያለው ጸሎት በጣም አስፈላጊው ገጽታ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መጸለይ ነው። የሚመለስ ጸሎት ማረጋገጫው እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ መፀለይ ብቻ ነው።

በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። 1 ዮሐንስ 5:14

ስለዚህ በሕይወት ውስጥ እንዲሆንልን ስለምንፈልገው ነገር የእግዚአብሔርን ፈቃድ የእግዚአብሄር ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅ በቂ   ጊዜ መውሰድ ይጠይቃል።

በሕይወታችን ረጅሙን ጊዜ ማሳለፍ ያለብን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማግኘት እና ለመረዳት መሆን አለበት፡፡ ቅድሚያ መስጠት ያለብን የእግዚአብሄርን ቃል ለመረዳትና እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን የልቡን ሃሳብ ለመረዳት መሆን አለበት፡፡

እግዚአብሄር በልቡ እና በነፍሱ እንዳለ ለመረዳት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ህብረትን እናድርግ፡፡ መንፈስ ቅዱስን በመጠበቅና በመስማት እግዚአብሄር ለአሁኑ ህይወታችን የሚፈልገውን ነገር ብቻ መፀለይ እንችላለን፡፡ 

እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ሮሜ 8:26

ረጅም ጊዜ የሚጠይቀውና በጣም ከባድ የሆነው የጸሎት ክፍል ስላለንበት የህይወታችን ሁኔታ እና ፍላጎት ከመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃሎች ማግኘት ነው።

አንዴ ለእኛ ያለውን የእግዚአብሄርን ልብ ከተረዳን ፍላጎታችንን በጸሎት መናገር ከሰከንዶች በላይ አይወስድም።

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

#ኢየሱስ #ጌታ #ፀሎት #ለምኑ #ብር #ብልፅግና #ስኬት #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment