Popular Posts

Friday, August 27, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 12

 


ፈውስን የመለማመጃው መንገድ እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን የፈውስ አላማ ከእግዚአብሄር ቃል መረዳት ነው፡፡ እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን የፈውስ ልብ ስንረዳ ፈውሳችንን መለማመድ እንችላለን፡፡

ፈውሳችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገረፍ ተሰርቶ አልቆዋል፡፡ አሁን ለፈውሳችን የሚያስፈልገው ነገር ስለፈውስ የእግዚአብሄርን ፈቃድ መረዳትና የእኛ የሆነውን በእምነት እጅ መቀበል ብቻ ነው፡፡

ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 2፡24

ሰዎች ለመዳን አግዚአብሄርን መጠበቅ የለባቸውም፡፡ እግዚአብሄር በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ደህንነትን ሰርቶ ጨርሶዋል፡፡ ሰው ደህንነትን በፈለገ ቁጥር እግዚአብሄር እንደ አዲስ የሚሰራው ደህንነት የለም፡፡ ሰው ለመዳን የሚያስፈልገው ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሰራውን ነገር መስማትና መቀበል ብቻ ነው፡፡

ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው። ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሮሜ 10፡8-9

በተመሳይ መልኩ ሰው በታመመ ቁጥር እግዚአብሄር ፈውስን እንደገና አይሰራም፡፡ እግዚአብሄር ብልጁ በኢየሱስ ክርሰሰቶስ መገረፍ ፈውስን ሰርቶ ጨርሶዋል፡፡ ሰው ለመፈወስ የሚያስፈልገው ክርስቶስ ስለፈውሱ የተገረፈውን መገረፍ በመረዳት ፈውሱን እርምጃ መውሰድ ብቻ ነው፡፡

ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል። ዮሐንስ 314-15

ፈውስ የሚደገፈው በእግዚአብሄር የፈውስ ፈቃድ ላይ ባለን እምነታችን ላይ ነው፡፡ እግዚአብሄር በኢየሱስ የፈውስ ነገራችንን ሰርቶ ቢጨርስም እኛ በእምነት እስካልተቀበልን ድረስ ፈውስ ሊሰራልን አይችልም፡፡ ኢየሱስ በምድር አገልግሎቱ ጊዜ ከእምነታችው ማነስ ምክኒያት ያልፈወሳቸው ሰዎች ነበሩ፡፡

በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም። ማቴዎስ 13፡58

በዚያም በጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በቀር፥ ተአምር ሊያደርግ ምንም አልቻለም። ማርቆስ 6፡5

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment