ሃጢያት ከእግዚአብሄር አይደለም፡፡
እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ
አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ። ማታም ሆነ
ጥዋትም ሆነ፥ ስድስተኛ ቀን። ዘፍጥረት 1፡31
እግዚአብሄር ሃጢያትን አልፈጠረም፡፡ እንዲሁም እግዚአብሄር በሽታን አልጠረም፡፡ ሃጢያትና በሽታ የመጣው ከሰይጣን ነው፡፡ ሰው በሰይጣን ተታሎ በሃጢያት እስራት ከወደቀ በኋላ ከበሽታ እስራል ላይ ወደቀ፡፡
ሰይጣን
የሚመጣው የሰዎችን ህይወት ሊሰርቅ ሊያርድና ሊያጠፋ ነው፡፡ ሰይጣን ከመስረቅ ፣ ማረድና ማጥፋት ውጭ ሌላ ምንም አላማ የለውም፡፡
ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ
ሌላ
አይመጣም፤ እኔ
ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሐንስ 10፡10
ኢየሱስ በምድር አገልግሎቱ የሰዎችን ነፍስ ከሃጢያት እስራት ለመፍታት እንዳገለገለ ሁሉ
በሃጢያት መክኒያት ወደምድር የገባውን የሰዎችንም በሽታ በትጋት ይፈውስ ነበር፡፡
ኢየሱስ ሰዎችን ከሃጢያት እስራት ለማላቀቅ ይሰብክ እንደነበር ሁሉ
ከበሽታቸው ለማላቀቅ በቅናት
ይፈውሳቸው ነበር፡፡
የኢየሱስን አገልግሎት በአጠቃላይ የኢየሱስን የምድር አገልግሎት ስናይ ለበሽታ የነበረን ጥላቻ እንመለከታለን፡፡ የኢየሱስን የምድር አገልግሎት ስናይ ሰዎችን
ከህመማቸው ለማላቀቅ በቅናት ሲያገለግል እንመለከታለን፡፡
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ
እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር
ነበረና፤ ሐዋሪያት 10፡38
ኢየሱስ
እንድም ቦታ ነፍሳችሁ ከዳነ ስጋዋ ባይፈወስም ችግር የለውም ሲል አንመለከተውም፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት
#አማርኛ #ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት
#ተስፋ #አሁን #ጌታ
#ሰላም #ደስታ #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ
#መናገር #ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment