Popular Posts

Wednesday, August 25, 2021

የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 10

 

 የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 10

ፈውስ የልጆች እንጀራ ነው፡፡ ፈውስ የልጆች መብት ነው፡፡ 

እርሱ ግን መልሶ፦ የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም አለ። ማቴዎስ 15፡26

ኢየሱስ ስለነፍሳችን ብቻ ሳይሆን ስለስጋችን ፈውስ ዋጋ ከፍሎዋል፡፡ 

ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። 1ኛ ጴጥሮስ 2፡24

በመሸም ጊዜ አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ፦ እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፥ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ። ማቴዎስ 8፡16-17

የታመመ ሰው ከበሽታው ጋር ከመኖር ይልቅ የቤተክርስትያን ሽማግሌዎችን እንዲጠራና ለፈውስ እንዲፀልዩለት መፅሃፍ ቅዱስ የሚያዘው ለዚህ ነው፡፡  

ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል። ያዕቆብ መልእክት 5፡14-15

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa 

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment