Popular Posts

Sunday, August 29, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 14

 


ለፈውስ እምነት ይጠይቃል፡፡ እኛ ብዙውን ጊዜ ራሳችንን ዝቅ አድርገን እንደምናየው እግዚአብሄር አያየንም፡፡ እግዚአብሄር የሚያየን እንደአብሮ ሰራተኛ አጋር ነው፡፡ ለፈውስ እምነት ይጠይቃል፡፡

እግዚአብሄር በኢየሱስ ክርስቶስ የሰራውን ለማየትና ለመጠቀም የእምነት እጅ ይጠይቃል፡፡ ፈውስን የምንቀበለው በእምነት ነው፡፡

ስለዚያም ነው ኢየሱስ ቃሉን ይሰብክ ነበር፡፡ ኢየሱስ በምድር አገልግሎቱ የእግዚአብሄርን ልብ ያሳይ ነበር፡፡ ኢየሱስ በምድር አገልግሎቱ እግዚአብሄርን ይተርከው ነበር፡፡

ፈውስን የሚያመጣው ለእኛ ያለውን የእግዚአብሄርን የፈውስ ፈቃድ መረዳት ስለሆነ በኢየሱስ የምድር አገልግሎት ዘመን ሰዎች ኢየሱስን ሊሰሙትና ሊፈወሱ ይመጡ ነበር፡፡

ከእነርሱም ጋር ወርዶ በተካከለ ስፍራ ቆመ፥ ከደቀ መዛሙርቱም ወገን ብዙ ሕዝብ ነበረ፥ ደግሞም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ከይሁዳ ሁሉ ከኢየሩሳሌምም ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ዳርም የመጡ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ሉቃስ 617

ኢየሱስ ኢየሱስ ስለሆነ ብቻ ከቃሉ ውጭ ምንም ሊያደርግላቸው አይችልም ነበር፡፡ ፈውስ ያለው የእግዚአብሄርን ሃሳብ በመረዳት ውስጥ ስለሆነ በኢየሱስ አገልግሎት ሰዎች ኢየሱስን ሊሰሙትና ሊፈወሱ ይመጡ ነበር፡፡

ወሬው ግን አብዝቶ ወጣ፥ ብዙ ሕዝብም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ይሰበሰቡ ነበር፤ ሉቃስ 515

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment