እምነት የጀብዱ ተጋድሎ ነው፡፡
እምነት ከምንም ነገር በላይ አስደሳች ጀብዱ ነው። የእምነት ጉዞ እውነተኛ ውድ ዋጋ ያለው ጀብዱ ነው። ከእምነት ጉዞ የበለጠ እጅግ አስደሳች ጀብደኝነት የለም።
እንግዲህ
ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና 2ኛ ቆሮንቶስ 5:7
እርሱን ከመጠየቃችን በፊት የሚያስፈልገንን የሚያውቅ እግዚአብሔርን ከመታመን የበለጠ ጀብደኝነት የለም።
ሳትለምኑት
አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። ማቴዎስ 6:8
ይህንስ
ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና። ማቴዎስ 6:32
በአካላዊ ዓይናችን የማይታየው የሚወደን አባታችን የእኛን ፍላጎት ያሟላል ብለን ከማመን የበለጠ ጀብደኝነት በምድር ላይ የለም።
የማይታየውን
እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 14፡17-18
ፍላጎቶቻችንን በወቅቱ ስለሚያሟላ እግዚአብሔርን አስቀድመን ከማመስገን ይልቅ ጀብደኝነት የለም።
እግዚአብሔር
እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። መዝሙር 23: 1
ምንም እንኳን የእኛን ፍላጎት ለማሟላት እግዚአብሄር
ሌሎች ሰዎችን ቢጠቀምም እግዚአብሔርን እንደ ዋና ምንጭ ከማመን የበለጠ እውነተኛ ጀብደኝነት የለም።
ለእርዳታ
ወደ ሌሎች ሰዎች ለመዞር ስንፈተን ዓይኖቻችንን በእሱ እና በእሱ ላይ ብቻ ከማተኮር የበለጠ ጀብደኝነት የለም።
የፈለገው
ይምጣ እንጂ በእርሱ ከመታመን የበለጠ ጀብደኝነት የለም።
እኛ በምንጠብቀው መንገድ የምንፈልገውን ካልሰጠን ፣ እርሱ ለእኔ ከእኔ በላይ ለእኔ ያስባል ብሎ ነገርህ ሁሉ በእርሱ ላይ ከመተው የበለጠ ጀብደኝነት የለም።
እግዚአብሄርን ለራሱ እንዲዋጋ በመተው እርፍ ከማለት የበለጠ ጀብደኝነት የለም።
እሱ እኛን እንደሚንከባከበን በማመን የሚያስጨንቀንን የህይወት ሃላፊነት በእሱ ላይ ከመጣል የበለጠ ጀብደኝነት የለም።
እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። 1 ጴጥሮስ 5:7
በአንዳች
ላለመጨነቅ ከመወሰን የተሻለ ጀብደኝነት የለም።
በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ፊልጵስዩስ 4:6-7
የኑሮ
ጥያቄውና ሸክሙ እያለን ፈገግ ከማለት የበለጠ እውነተኛ ጀብደኝነት የለም።
ከላይ ከሚመጣው መልካም ነገር ሁሉ ምንጊዜም ጥሩ እና ጥሩ ብቻ መሆኑን
ከማመን በላይ ምንም የሚያስደስት እና የሚያስፈጠነዝ ጀብደኝነት የለም።
ወይስ ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው? ማቴዎስ 7:9 - 11
ደሞዛችንን ፣ ቁጠባችንን
ወይም የንግድ ሥራችንን ገቢ ግምት ውስጥ ሳያስገባ እግዚአብሔርን ከመጠየቅ የበለጠ ጀብደኝነት የለም።
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥
የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ማቴዎስ 7፡7-8
የምንፈልገው
ነገር በእጃችን በሌለ ጊዜ እና ነገሩን ለማግኘት በእኛ አቅም በማንይቻልበት ጊዜ በእውነት እግዚአብሄረን እንለምናለን፡፡ ማድረግ የምትችለውን ነገር ለማድረግ ከቻልክ ማቀድ እንጂ መለመን አይባልም።
'በዚህ ፈትኑኝ' የሚለውን የእግዚአብሔርን ግብዣ ከመታመን የበለጠ የሚያስደስት ነገር የለም።
የሰማይንም
መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ሚልክያስ 3:10
ይህ
እግዚአብሔርን እንደገና ለመፈተን ወርቃማ ዕድል ነው።
በማየት
ሳይሆን በእምነት ከመራመድ የበለጠ ጀብደኝነት የለም።
ታዲያ
እምነት ለእንደዚህ ዓይነት ጊዜ ካልረዳህ ለመቼ ሊሆንህ ነው?
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ መጣጥፎች
https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
#እግዚአብሔር #ኢየሱስ #እውቀት #ጀብድ #ጀብዱ #እምነት #ፍቅር #ጋብቻ #ጽናት #መታመን #ጸጋ #ማዳን #ቤተ ክርስቲያን #ምስክርነት #ደስታ #ስብከት #መጽሐፍ ቅዱስ #ማቴዎስ #አቢይዲንሳ #ቅዱሳትመጻሕፍት #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment