Popular Posts

Monday, August 30, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 15

 

እግዚአብሄር የታመሙትን በመፈወስ የታወቀ አምላክ ነው፡፡

እግዚአብሔርም ሕማምን ሁሉ ከአንተ ያርቃል፤ የምታውቀውንም ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ በአንተ ላይ አያደርስብህም፥ በጠላቶችህም ሁሉ ላይ ያመጣባቸዋል። ዘዳግም 7፡15

እግዚአብሄር ሰዎች  እንዲወጡ ፣ እንዲገቡ ፣ እንዲሰሩ እና እንዲኖሩ ስለፈጠራቸው ሊያደክማቸው ሊያሳምማቸው እና የሚመጣውን ደዌንና ህማምን በመፈወስ ይታወቃል፡፡

ቃሉን ላከ ፈወሳቸውም፥ ከጥፋታቸውም አዳናቸው። መዝሙር 107፡20

እግዚአብሄር የቆሰሉትን በመፈወስ ይታወቃል፡፡

ልባቸውን የቈሰሉትን ይፈውሳል፥ ሕማማቸውንም ይጠግናል። መዝሙር 147፡3

እግዚአብሄር የተሰበሩትን በመጠገን የታወቀ አምላክ ነው፡፡

እኔ ጤናህን እመልስልሃለሁ ቍስልህንም እፈውሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር ማንም የማይሻት፥ የተጣለች ጽዮን ብለው ጠርተውሻልና። ኤርሚያስ 30፡17

እግዚአብሄር የፈውስ አምላክ ነው፡፡

የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፦ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። ሉቃስ 4፡17-19

በኢየሱስ አገልግሎትም የተተረከው የእግዚአብሄር የፈውስ ቅናት ነው፡፡

እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤ ሐዋሪያት 10፡38

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment