Popular Posts

Tuesday, August 17, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 2

 

እግዚአብሄር በሰዎች ብርታትና ጤንነት ደስ ይለዋል፡፡

እግዚአብሄር ከማናችንም ጋር አይፎካከርም፡፡ እግዚአብሄር ከማናችንም ጋር እልኽ ውስጥ አይገባም፡፡ እግዚአብሄር የማናችንም ጤንነት አያስቀናውም፡፡

እግዚአብሄር በመጀመሪያም የፈጠረን ለብርታትና ለጤንነት ስለሆነ ስንወጣ ስንገባ ስንሰራ ፍሬያማ እና ምርታማ ስንሆን ደስ ይለዋል፡፡

የጤንነታችን አንደኛ ደጋፊ እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡

እግዚአብሄር በሽታን በሁሉም አቅጣጫ ይቃወመዋል፡፡ እግዚአብሄር ሰዎች በቃሉ ሲያምኑ እንዲፈወሱ የፈውስን ቃል አዘጋጅቶዋል፡፡

ክርስቶስን የሚከተሉ ሰዎች ሲታመሙ የሚፈወሱበትን መንገድ ጌታ አዘጋጅቶዋል፡፡

ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታም ስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታም ያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል። ያዕቆብ 5፡14-15

ሰዎች የፈውስን ቃል ከመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ፈልገው ሲያገኙና ሲያምኑ የእግዚአብሄር ፈውስ በመለኮታዊ አሰራር የእግዚአብሄር ፈውስ በህይወታቸው ያልፋል፡፡

እግዚአብሄር ተአምራዊ የፈውስን ስጦታ ብቻ ሳይሆን ሰዎች በሳይንሳዊ ህክምና ከበሽታቸው እንዲገላገሉ በየዘመናቱ እግዚአብሄር ለባህላዊና ለዘመናዊ የህክምና ባለሙያዎች ጥበብን ይሰጣል፡፡

እግዚአብሄር በሽታን የሚዋጋው አንድም ሳያስቀር በሁሉም ግንባር ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment