የእስራኤል ህዝብ የእግዚአብሄር ብቸኛ ህዝብ ነበሩ፡፡
እግዚአብሄር የእስራኤልን ህዝብ የያዘበትን መንገድ በመመልከት እግዚአብሄር ህዝቡን እንዴት እንደሚይዝና እንደሚንከባከብ መመልከት
ይቻላል፡፡
የእስራኤል ህዝብ በበደላቸው ምክኒያት እባብ በነደፋቸው
ጊዜ እንኳን እግዚአብሄር እነርሱን የሚፈልግበትን መንገድ ከመፈለግ አላቆመም፡፡
ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው። ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፤ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ። ዘኍልቍ 21፡8-9
እግዚአብሄር በየጊዜው እንዴት ራሳቸውን በጤንነት
እንደሚይዙ እና ጤንነታችውን ካጡትም አንዴት መልሰው እንደሚፈወሱ በነቢያቶቻቸው በኩል ያስተምራቸው ነበር፡፡
ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሌም ጆሮህን አዘንብል። ከዓይንህ አታርቃት፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃት። ለሚያገኙአት ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና። ምሳሌ 4፡20-22
እነሆ፥ ፈውስንና መድኃኒትን አመጣላታለሁ፥ እፈውሳቸውማለሁ፤ የሰላምንና የእውነትን ብዛት እገልጥላቸዋለሁ። ኤርሚያስ 33፡6
አቤቱ፥ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ፤ አድነኝ እኔም እድናለሁ፤ አንተ ምስጋናዬ ነህና። ኤርሚያስ 17፡14
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት
#ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ
#ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #ልብ
#እምነት #ተስፋ
#አሁን #ጌታ
#ሰላም #ደስታ
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment