Popular Posts

Wednesday, August 18, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 3

 

እግዚአብሄር በእስራኤላዊያን ብርታትና ጤንነት ደስ ይለው ነበር፡፡

ሰው ምግቡን እና የሚጠጣውን ካስተካከለ ምግብን በማስተካል ብቻ አብዛኛውን በሽታ መከላከልና መቋቋም እንደሚቻል ሳይንስ ያስተምራል፡፡ ምክኒያቱም የምንበላው ምግብ እና የምንጠጣው መጠጥ ለጤንነታችን ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል እንዲሁም የምብላውነማ የምንጠጣው ጤንነታችንን ሊያውክ ይችላል፡፡

እግዚአብሄር የምንበላውንና የምንጠጣውን ከባረከ ምግቡና መጠጡ ይስማማናል ፣ ጤንነታችንን ያበዛዋል እንዲሁም በሽታ የመከላከል አቅማችንን በእጅጉ ያሳድገዋል፡፡

አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ታመልኩታላችሁ፥ እርሱም እህልህንና ውኃህን ይባርካል፤ በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ። ዘጸአት 23፡25

በብሉይ ኪዳን እስራኤላዊያን የእግዚአብሄር ብቸኛ ህዝብ ነበሩ፡፡ እግዚአብሄር ከእስራኤላዊያን ጋር የነበረው ግንኙነት በመመልከት እግዚአብሄር ከህዝቡ ጋር ስላለው ግንኙነት እግዚአብሄር ስለ ህዝቡ ፈውስ እና ጤንነት ብዙ ነገር መማር ይቻላል፡፡

እግዚአብሄር ስለ ጤንነታችን ግድ ይለዋል፡፡

እስራኤላዊያን ከግብፅ ሲወጡ በመካከላቸው አንድም በሽተኛ አለመኖሩ እግዚአብሄር ለህዝቡ ጤንነት እና ጥንካሬ ምን ያህል ግድ እንደሚለው ያሳያል፡፡  

ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው፥ በወገናቸውም ውስጥ ደዌ አልነበረም። መዝሙር 105፡37

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment