Popular Posts

Tuesday, August 24, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 9

 

እግዚአብሄር የፈጠረው ፍጥረት ሁሉ መልካም ነበር፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በነፍስም በስጋም ሙሉ አድርጎ ነው፡፡

በሰንበትም በአንድ ምኵራብ ያስተምር ነበር። እነሆም፥ ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ የድካም መንፈስ ያደረባት ሴት ነበረች፥ እርስዋም ጐባጣ ነበረች ቀንታም ልትቆም ከቶ አልተቻላትም። ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና። አንቺ ሴት፥ ከድካምሽ ተፈትተሻል አላት፥ እጁንም ጫነባት፤ ያን ጊዜም ቀጥ አለች፥ እግዚአብሔርንም አመሰገነች። የምኵራብ አለቃ ግን ኢየሱስ በሰንበት ስለ ፈወሰ ተቈጥቶ መለሰና ሕዝቡን፦ ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ እንግዲህ በእነርሱ መጥታችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት አይደለም አለ። ጌታም መልሶ፦ እናንተ ግብዞች፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በሰንበት በሬውን ወይስ አህያውን ከግርግሙ ፈትቶ ውኃ ሊያጠጣው ይወስደው የለምን? ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? አለው። ሉቃስ ወንጌል 1310-16

ከምናስበው በላይ ብዙ ነገር መንፈሳዊ ነው፡፡ ዶክተሮች በመንፈሳዊ አለም ሊገልፁት ስለማይችሉ የዲስክ መንሸራተት ነው ሊሉ ይችላሉ፡፡ ጌታ ግን ከስጋዊው አለም አሻቅቦ መንፈሳዊውን አለም ስለሚያይ ሰይጣን ያሰራትን አለ፡፡

ከብዙ ጥቃቶች ጀርባ ሰይጣን ዲያቢሎስ አለ፡፡ ሰይጣን ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋ እንጂ ስለሌላ አይመጣም፡፡

ስለዚህም ነው ኢየሱስ በምድር በተመላለሰ ጊዜ በታላቅ ቅናት የዲያቢሎስን ስራ ያፈርስ የነበረው፡፡

ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። 1ኛ ዮሃንስ 3፡9

እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤ ሐዋሪያት 10፡38

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment