Popular Posts

Monday, August 16, 2021

የአርባ ቀን የፈውስ ትምህርት ጉዞ ቁጥር 1

 


እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በጤንነት ነው፡፡

ስለማንኛውም ነገር ከስር መሰረቱ ለማጥናት ከጥንት ምን እንደነበረ ማጥናት ጠቃሚ ግንዛቤን ይሰጣል፡፡ ካለ መጀመሪያና ካለጥንቱ እውቀት ያለውን እውቀት ሙሉ ሊሆን አይችልም፡፡

ስለ እግዚአብሄር ፈቃድ በተነሳ ጥያቄ የጠቀሰላቸው ከጥንት የነበረውን የእግዚአብሄርን ኦሪጅናል ሃሳብ ነው፡፡

እርሱም፦ ሙሴስ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ፤ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም። ማቴዎስ 198

እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጠር ያለው የእግዚአብሄር ሃሳብን መከተል ከብዙ ስህተት ያድነናል፡፡ ሰው በጤንነት እንዲገባና እንዲወጣ  እግዚአብሄር በልቡ ስላለው ፈቃድ ለማወቅ ከጥንት የነበረውን የእግዚአብሄርን ኦሪጅናል የፍጥረት ሃሳብ እንመልከት፡፡

እግዚአብሄር ፍጥረትን ከፈጠረ በኋላ መልስ ብሎ ሲያይና ሲገመግም ያየው ነገር መልካም እንደሆነ ነው፡፡

እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፥ ዘፍጥረት 14

እግዚአብሔርም መልካም እንደ ሆነ አየ። ዘፍጥረት 110

እግዚአብሔርም መልካም እንደ ሆነ አየ። ዘፍጥረት 112

በቀንም በሌሊትም እንዲሠለጥኑ፥ ብርሃንንና ጨለማንም እንዲለዩ፤ እግዚአብሔርም መልካም እንደ ሆነ አየ። ዘፍጥረት 118

እግዚአብሔርም ታላላቆች አንበሪዎችን፥ ውኃይቱ እንደ ወገኑ ያስገኘቻቸውንም ተንቀሳቃሾቹን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፥ እንደ ወገኑ የሚበሩትንም ወፎች ሁሉ ፈጠረ፤ እግዚአብሔርም መልካም እንደ ሆነ አየ። ዘፍጥረት 121

እግዚአብሄር ሰውን ደካማ የማይንቀሳቀስ የማይወጣ የማይሰራ የማይወርድ አድርጎ በፍፁም አልፈጠረውም፡፡

እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው በምድር ላይ እንዲገባ እንዲወጣ በጥንካሬ እንዲወክለው ነው፡፡

በሰው ፍጥረት ውስጥ በሽታ እንግዳ ነገር ነው፡፡

በሰው ብርታት ሙላት እና ጤንነት እንጂ በሰው ድካም እጦትና ህመም እግዚአብሄር አይከብርም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #ፈውስ #ስጋ #ጤንነት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ተስፋ #አሁን #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment