የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፥ ማቴዎስ 26:24
በዚያን ጊዜ፦ እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ አልሁ ይላል። ዕብራውያን 10፡7
ሰው ለእግዚአብሄር ክብር ተፈጥሮአል፡፡ ሰው በሚያስበው በሚናገረው እና በሚያደርገው ነገር ሁሉ እግዚአብሄርን እንዲያከብር ለእግዚአብሄር ክብር ተፈጥሮአል፡፡
እያንዳንዱ ሰው ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት በምድር ላይ እንዲያደርግ ታልሞና ታቅዶ የፈጠረበት አላማ አለ፡፡ እያንዳንዱ ሰው ወደምድር የሚመጣው በእግዚአብሄር አስቀድሞ የተዘጋጀለትን አላማ ለመፈፀም ነው፡፡
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10
ይህን የእግዚአብሄር ፈቃድ እንዳይሆን የሚገዳደሩ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ነገር ግን በመጨረሻ የሚሆነው የእግዚአብሄር ፈቃድ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ሃሳብ ሊያሰናክል የሚችል ሃይል የለም፡፡ የእግዚአብሄርን ሃሳብ መንገድ ሊያስቀይስ የሚፈልግ ብዙ ነገር አለ፡፡ የመጨረሻውን የእግዚአብሄርን ሃሳቡን ሊያግድ የሚል ሃይል የለም፡፡
በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፤ የእግዚአብሔር ምክር ግን እርሱ ይጸናል። ምሳሌ 19፡21
ስለዚህ ነው ሰው የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግ ራሱ እስከሰጠ ድረስ የእግዚአብሄር ፈቃድ በህይወቱ እንደሚፈፀም በእግዚአብሄር አሰራር ማመን አለበት፡፡
ሰው ራሱ ለእግዚአብሄር ሃሳብ እንቅፋት ለመሆን እስካልወሰነ ድረስ በህይወቱ የእግዚአብሄርን ምክር ሊያስተጓጉል የሚችል ምንም ሃይል የለም፡፡
ሰው የእግዚአብሄርን ፈቃድ በህይወቱ እንዲደረግ እየፈለገ ፈቃዱ እንዳይሆን የሚያገደው ምንም ሃይል የለም፡፡
ሰው በተለያዩ ነገሮች ውስጥ ያልፋል፡፡ ሰው በብዙ ከፍታና ዝቅታ ውስጥ ያልፋል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄርን ለሚወድ ሰው እንደሃሳቡም ለተጠራ ሰው ነገር ሁሉ የሚሰራው ለበጎነቱ ነው፡፡ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ጉዞው የሚጠናቀቀው የሚሆነው የእግዚአብሄር ፈቃድ ነው፡፡
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8፡28
የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል፥ ማቴዎስ 26:24
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
#የእግዚአብሄርምክር #የእግዚአብሔርፈቃድ #እግዚአብሔር #እንደተፃፈ #እምነት #የሰውአሳብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment