ውድ
ወላጆች
የልጆችዎ
ፈተናዎች በቅርቡ ይጀመራል፡፡ ለልጅዎ ደህና ውጤት እንደሚፈልጉ
አውቃለሁ፡፡
ነገር
ግን እባክዎን ይህንን አይርሱ፡፡ ለፈተናው ከተቀመጡት ተማሪዎች መካከል ሂሳብን መረዳት የማይፈልግ አርቲስቶች አሉ፡፡ ለፈተናው ከተቀመጡት ተማሪዎች መካከል ስለ ታሪክ ወይም የእንግሊዘኛ ሥነ-ጽሑፍ ግድ የማይሰጠው ሥራ ፈጣሪዎች ወይም ነጋዴዎች አሉ፡፡ ለፈተናው ከተቀመጡት ተማሪዎች መካከል የኬሚስትሪ ውጤታቸው ምንም የማያመጣላቸው
ሙዚቀኞች አሉ፡፡ ከፊዚክስ ፈተና ውጤታቸው
የበለጠ አካላዊ ብቃታቸው አስፈላጊ የሆነ አትሌቶች
አሉ፡፡
ልጅዎ
ከፍተኛ ውጤት የሚያመጣ ከሆነ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ ውጤት ካላመጡ እባክዎን
በራስ የመተማመን ስሜታቸውንና ክብራቸውን መንካት የለብዎትም፡፡
መልካም ይሁን በሉዋቸው፡፡ ይህ
ፈተና ብቻ ነው! በህይወት ውስጥ በጣም ወሳኝ በሆኑ በርካታ ክህሎቶች ተክነዋል፡፡ ምንም ውጤት ቢያመጡ ይወደዱዋቸው አይፍረዱባቸው፡፡
እባክዎ
ይህን ያድርጉ፡፡ ልጆችዎ በምንም ሁኔታ ውስጥ ካበረታቷቸው
ዓለምን ሲያሸንፉ ይመለከታሉ፡፡ አንድ ፈተና ወይም ዝቅተኛ ውጤት ህልማቸውን እና
ችሎታዎቻቸውን አያጠፋውም፡፡ እባክዎ በአለም ውስጥ ብቸኛ ደስተኛ ሰዎች ዶክተሮች እና
ኢንጂነሮች ብቻ ናቸው ብለው አያስቡ፡፡
በታላቅ አክብሮት
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ክህሎት #ስጦታ #የእግዚአብሔርፈቃድ #እግዚአብሔር #ጥሪ #እንደተፃፈ #እምነት
#የሰውአሳብ #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#መንፈስቅዱስ #ህይወት
#ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment