በአለም ላይ ያለው ችግር ሁሉ ምንጩ የማንነት
ጥያቄ አለመመለስ ነው፡፡ ሰው ለራሱ ያለው አመለካከት ሲዛባ ለእግዚአብሄር ፣ ለሰውና ለህይወት ያለው አመለካከት ሁሉ ይዛባል፡፡
ሰው እግዚአብሄር እንደፈጠረው እንደዚያው አድርጎ
ራሱን ማየት ሲጀምር የህይወት ጥያቄዎቹ ሁሉ መመለስ ይጀምራሉ፡፡ ሰው እግዚአብሄር እንደፈጠረው ራሱን ሲያይ ለእግዚአብሄር ክብር
ብቻ መኖር ይጀምራል፡፡ ሰው ማን እንደሆነ ሲረዳ እንደ እግዚአብሄር ማየት ይጀምራል፡፡ ሰው ማንነቱን ሲረዳ ወደፊት እንዳይሄድ
ያገዱት መሰናክሎች ሁሉ ከፊቱ መነሳት ይጀምራሉ፡፡ ሰው ማን እንደሆነ ሲረዳ ከእግዚአብሄር ጋር ይራመዳል፡፡
ሰው ማንነቱን ካልተረዳ ሁሉም ነገር ይደበላለቅበታል፡፡
ሰው እግዚአብሄር እንደሚያየው ራሱን ካላየ ለሰው ፣ ለራሱ እና ለህይወት ያለው አመለካከት ይዛባል፡፡ ሰው ማንነቱን ካላወቀ የሚኖረው
እውቀት ሁሉ የተበላሸ ይሆናል፡፡
እግዚአብሄር የፈጠረው ሰው በሰላም ይኖር ነበር፡፡
ሰው ሰላሙን ያጣው የማንነት ጥያቄ በተነሳ ጊዜና የማንነቱን እውቀት ከተሳሳተ ቦታ በፈለገና ስለማንነቱ በተሳሳተ ጊዜ ነው፡፡
ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ። ዘፍጥረት 3፡5
ሰው ለእግዚአብሄር ክብር ታቅዶ የተፈጠረ ስለሆነ
ሰው ስለማንነቱ ከእግዚአብሔር ውጭ ማንም ሊነግረው አይችልም፡፡ ሰው ስለማንነቱ ከእግዚአብሄር ቃል ውጭ ከየትም ቢሰማ ይስታል፡፡
ሰው የሚያርፈው ስለማንነቱ እግዚአብሄር በቃሉ
ሲነግረው ብቻ ነው፡፡ ሰው የሚያፈራው ስለማንነቱ ያለው መረዳት ሲጨምር ነው፡፡ ሰው እግዚአብሀር እንደሚያየው ራን ሲያይ ብቻ ነው
ህይወትን በአግባቡ መያዝ የሚችለው፡፡ ሰው ስለማንነቱ ያለው ትክክለኛ መረዳት ከእግዚአብሄር ጋር ፣ ከራሱ ጋርና ከሰው ጋር ሰላምን
ይሰጠዋል፡፡
ሰው ስለማንነቱ ሲረዳ ህይወት ይጣፈጠዋል፡፡ ሰው
ስለማነነቱ ሲረዳ አገልግሎ አይጠግብም፡፡ ሰው ስላምነነቱ ሲረዳ ለእግዚአብሄርና ለእግዚአብሄር ብቻ ለመኖር ይቀናል፡፡
ወይስ መጽሐፍ፦ በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን? ያዕቆብ 4፡5
ስለማንነቱ የተረዳ ሰው ዝቅ ብሎ የእግዚአብሄርን
ህዝብ ለማገልገል አይቸግረውም፡፡ በእግዚአብሄር ዘንድ ያለውን የክብር ከፍታ የተረዳ ሰው ምንም ዝቅታ ሊያወርደው እንደማይችል ስለሚያውቅ
በነፃነት ይኖራል ያገለግላል፡፡
ኢየሱስ አብ ሁሉን በልጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥ ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።
ዮሐንስ 13፡3-5
ስለማንነቱ ትክክለኛ እውቀት ያለው ሰው ራሱን
ከውድድር እና ከአለም ፉክክር ያገላል፡፡ ስለማንነቱ የተረዳ ሰው በዝና በክብር በሃብት ራሱን ከፍ ለማድረግ ሲጥር አይታይም፡፡
ማንነቱን የተረዳ ሰው እግዚአብሄርን የማያውቁ ሰዎች የሚያከብሩትንና ዘመናቸውን የሚያባክኑበትን ነገር ይንቃል፡፡
ኢየሱስም፦ ለቀበሮዎች ጕድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው። ሉቃስ 9፡58
ስለማንነቱ ትክክለኛ እውቀት ያለው ሰው በእግዚአብሔር
ብቻ ረክቶ ይኖራል፡፡ ስለማንነቱ የተረዳ ሰው ከእግዚአብሄር ውጭ ሌላ የሚያረካው የሚፈልገውና የሚያሳድደው ነገር የለም፡፡
እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ። መዝሙር 17፡15
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #በክርስቶስ #መንፈስ #ማንነት
#መልክ #አምሳል #የእግዚአብሄርልጅ #ክብር #ቤተክርስትያን #አማርኛ
#ማየት #የእግዚአብሄርመንግስት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አዲስፍጥረት #ክርስቶስ #የእግዚአብሄርቤተሰብ
#ማእረግ #ስልጣን #ከፍታ
No comments:
Post a Comment