በቅዱስ
ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤
ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።መዝሙር 105፡3-4
በምድር ላይ እንደተጠበቁት የማይገኙ ብዙ ነገሮች
አሉ፡፡ በጠበቅንባቸው ስላላገኘናቸው ብዙ ነገሮች ያሳዝኑናል ቅር ያሰኙናል፡፡ ሰዎች ብዙ ነገሮችን ጠብቀው በብዙ ነገሮች ይሰናከላሉ
ያዝናሉ ይዝላሉ ተስፋም ይቆርጣሉ፡፡
ብዙ ነገሮች ካቅማቸው በላይ ተስፋ አድርገንባቸው
ያሳዝኑናል፡፡
ነገር ግን እግዚአብሄርን መፈልግ ግን አስተማማኝ
ነገር ነው፡፡ እግዚአብሄን መፈለግ መቼም አያከስርም፡፡ እግዚአብሄርን መፈለግ መቼም አይፅትም፡፡
እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሰው የማያሳዝንና የማያሰናክል
አስተማማኝ ነገርን መርጧል፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሰው ግን ተስፋው አይጠፋም አይሰናከልም አያዝንም፡፡
እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሰው ይፀናል ይበረታል
ያሸንፋል፡፡ እግዚአብሄርን እንድመፈለግ አስተማማኝ ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄርን እንደመፈለግ አትራፊ ስራ የለም፡፡ እግዚአብሄርን
እንደመፈለግ የሚያስመካ ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄርን እንደመፈለግ የሚያጓድድ ነገር የለም፡፡
እግዚአብሄርን እንደሚፈልግ ሰው ደስተኛ ሰው የለም፡፡
እግዚአብሄርን እንደሚፈልግ ሰው አትራፊ ሰው የለም፡፡ እግዚአብሄርን
እንደሚፈልግ ሰው ስኬታማ ሰው የለም፡፡ ባለጠጋውን እግዚአብሄርን እንደመፈለግ የመሰለ ባለጠግነት የለም፡፡ እግዚአብሄርን እንደመፈለግ
አስደሳች ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄርን እንደመፈልግ ጥበብ የለም፡፡
ምክሩ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉት ነው፡፡
ሁሌ ለመሳካት ፣ ሁሌ ለመከናወን ፣ ሁሉ ለማሸነፍ
፣ ሁሉ ለመፅናት ሁልጊዜ ፊቱ መፈለግ፡፡
በቅዱስ
ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።መዝሙር 105፡3-4
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ፀሎት #ሁሉንቻይ #ጥበኛ #ሁሉበሁሉ #እግዚአብሔር #እግዚአብሔርንመፈለግ #ፀሎት #የዘላለምህይወት #የእግዚአብሔርፈቃድ #የጊዜው #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና #አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment