Popular Posts

Monday, November 13, 2017

አስሩ የእይታ ደረጃዎች

እግዚአብሄር እንደሚያይ የሚያይ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ይራመዳል፡፡ እንደ እግዚአብሄር የማያይ ስው በጨለማ ውስጥ ይመላለሳል፡፡ እንደ እግዚአብሄር የማያይ ለብዙዎች ጥቅም በውስጡ እግዚአብሄር ያስቀመጠውን ታላቅ እምቅ ጉልበት ሳይጠቀምና ፍሬ ሳያፈራበት ተራ ሰው ሆኖ ህይወቱን ያባክናል፡፡ እይታችን ከፍታችንን ይወስነዋል፡፡ እይታችን ነፃነታችንን ይወስናል፡፡ እይታችን ፍሬያማነታችንን ይወስናል፡፡  
1.      አሁን ያለበትን አለማየት ከየት እንደመጣን ማስተዋል
ሰው ከዘላለም ሞት እንደዳነ ካልረሳው ለእግዚአብሄር በሚገባ ኖሮ ማለፍ ይችላል፡፡ ሰው ከምን አይነት ውድቀትና አደጋ እንደዳነ በትክክል ካየ ትጋቱ ይጨምራል፡፡ ሰው ከምን አይነት ጥፋት እንደዳነ ካልረሳው እግዚአብሄርን በሁሉ ያመሰግናል፡፡ ሰው ከምን አይነት ጥፋት ውስጥ እንደዳነ ካወቀ ለትጋርት ጉልበት ያገኛል፡፡ ሰው ከምን እይነት አሰቃቂ ቦታ እንዳመለጠ ካወቀ ሰዎችን የሚያምሩዋቸውና ከመንገዳቸው የሚያሰናክሉዋቸው ተራ ነገሮች አያምሩትም፡፡
እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል። 2ኛ ጴጥሮስ 1፡9
2.     የቅርቡን አለማየት የሩቁን ማየት
እንደ ክርስትያን አርቆ ማየት ያለበት ሰው የለም፡፡ ክርስትና ከዘላለማዊ አምላከ ጋር ያለ ግንኙነት ነው፡፡ ክርስትያን የሚኖረው ለዘላለም ነው፡፡ ክርስትያን በሚያደርገው በእያንዳንዱ ነገር ከጊዜያዊ እይታ አልፎ በእግዚአብሄር የዘላላም እቅድ ውስጥ ያለውን ድርሻ መመልከት አለበት፡፡ ክርስትያን አንደ ሰው ኖረው እንደሰው አንደሚሞቱት ሰዎች አያይም፡፡ የክርስትያን እይታ ሰው ብቻ ሆኖ እንዳያልፍ ያደርገዋል፡፡
እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን? 1 ቆሮንቶስ 3፡1፣3
3.     አካባቢን አለመመልከት ኢየሱስን መመልከት
ሰው አሁን ያለውን ጊዜያዊውን ችግር ካይ ካተኮረና አይኑን ከኢየሱስ ላይ ካላተኮረ ሩቅ መሄድ ያቅተዋል፡፡ ሰው በጊዜያዊ ደስታ ላይ ለካተኮረ ዘለቄታዊ ነገርት ማድረግ ያቅተዋል፡፡ ሰው እይታው በአሁን ላይ ብቻ ከሆነ ቋሚ ክብር ያለው ነገር ማድረግ ያቅተዋል፡፡
የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። ዕብራውያን 12፡1-2
4.     የሚታየውን አለማየት የማይታየውን ማየት
ሰው የሚታየውን ብቻ ካየ በእግዚአብሄር ቃል መኖር አችልም፡፡ ሰው የሚታየውን ብቻ ካየ በእምነት እግዚአብሄን ደስ ማሰኘት አይችልን፡፡ ሰው የማይታየውን ካላየ በማይታየው በእግግዚአብሄር መንግስት ፍሬያማ መሆን አይችልም፡፡
ሰው በላይ ያለውም ካላየ ውጤታማ ቸአይሆንም፡፡
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18
5.     ምድራዉን ብቻ አለማየት ሰማያዊውን ሃገር ማየት
ሰው በምድር ላይ ጊዜያዊ እንደሆነ ካወቀ እግዚአብሄር የሚፈልገው ኑሮ ይኖራል፡፡ ሰው የምድር ላይ ኑሮውን እንደ እንግድነት ካላየው እግዚአብሄርን ሊያስደስት አይችልም፡፡ ሰው በምድር ላይ እንደጊዜያዊ ተላላፊ ካልኖረ ለእግዚአብሄር ኖሮ ማለፍ አይችልም፡፡ 
ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ 3፡1-2
መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ ፊልጵስዩስ 3፡19-20
6.     የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን ጌታ ማየት
ክርስትያን ጌታው በልቡ ነው፡፡ ክርስትያን የሚፈራው የማይታየውን ጌታ እንጂ የሚታዩትን የአካባቢውን ሁኔታዎች አይደለም፡፡ ክርስትያን የሚከተለው በነውስጡ የሚመራውን ክርስቶስን ነው፡፡ የሰው ተስፋ በውስጡ የሚኖረው ክትስቶስ ነው፡፡  
ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። 1ኛ ጴጥሮስ 3፡15
ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው። ቆላስይስ 1፡27
የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ። ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምትገዙ በትጋትና በበጎ ፈቃድ ተገዙ፤ ኤፌሶን 6፡6-7
7.     የሚታየውን ሁኔታ ሳይሆን የማይታየውን የእግዚአብሄርን ቃል ተስፋ ማድረግ
ክርስትያን የሚያየው የእግዚአብሄርን ቃል ነው፡፡ ክርስትያን የሚያምነው የእግዚአብሄርን ቃል ነው፡፡ ክርስትያን የሚያተኩረው በእግዚአብሄር ቃል ላይ ነው፡፡ ክርስትያን ህይወቱን የሚገነባው በእግዚአብሄር ቃል ላይ ነው፡፡ ክርስትያን  በአካባቢው ከሚታዩ ነገሮች ሁሉ ይልቅ በአይን የማይታየውን የእግዚአብሄርን ቃል ነው የሚከተለው፡፡
ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ። የመቶ ዓመትም ሽማግሌ ስለ ሆነ እንደ ምውት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ፤ ሮሜ 4፡18-19
8.     ሰው ምድራዊውን ስጋ ሳይሆን ሰማያዊውን መንፈስ ያያል
ሰው በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረውን መንፈሱን ካላየ ለእግዚአብሄር ሊኖር አይችልም፡፡ ሰው የማይታየውን ማንነቱን ካላየ በእግዚአብሄር መልክና አምሳል መፈጠሩን አይረዳም፡፡
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና። ነገር ግን በስጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን፥ ምን እንድመርጥ ኣላስታውቅም። ፊልጵስዩስ 1፡22-23
ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ዮሃንስ 3፡5
ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡16
9.     ምድራዊው ሳይሆን ሰማያዊውን ሽልማት ማየት
ሰው ለምድራዊው ሽልማት ቦታ ከሰጠ ለሰማያዊው ለማያልፈው ሽልማት ቦታ አይኖረውም፡፡ ሰው በምድራዊ ፉክክርና ውድድር ከተያዘ የሰማያዊውን ሩጫ በትግስት መሮጥ ያቅተዋል፡፡
የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን። 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡25
10.    በምድራዊው ሳይሆን በሰማዩን መዝገብ ማከማቸት
ሰው በምድር የሚያገኘውን ማንኛውንም ነገር እንዴት በሰማይ መዝገብ እንደሚያስመዘግበው ካላሰበ ይከስራል፡፡ በጊዜያዊ ገንዘብ ዘላለማዊ ውጤት የሚያገኝ ሰው ጥበበኛ ሰው ነው፡፡  
እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16፡9
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እይታ #ተስፋ #መፀለይ #መንፈስ #በረከት #መዝገብ #ሰማይ #እንግዶች #ዘላለም #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #እምነት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እይታ #ምድራዊ #ሰማያዊት #ማየት #ቅርብ

No comments:

Post a Comment