መርገም አለመሳካት አለመከናወን ማለት ሲሆን መርገም
በቀላሉ የበረከት ተቃራኒ በተፈጥሮአዊው አለም ላይ ተፅእኖ የሚያደርግ ልእለ ተፈጥሮአዊ ሃይል ነው፡፡
አንዳንዴ አንድን ነገር ከመተርጎም ይልቅ ተቃራኒውን
ነገር መተርጎም የተሻለ መረዳት ይሰጣል፡፡ የመርገም ተቃራኒ በረከት ሲሆን በረከት ማለት ደግሞ ደስተኝነት ፣ እምቅ ጉልበት ፣
ሞገስ ፣ የተመሰገነ ፣ የታጠቀ ፣ የተለቀቀ ማለት ነው፡፡
ሰው
ሲፈጠር ተባርኮ ነው የተፈጠረው፡፡ ሰው እንዲወጣ እንዲገባ እንዲበዛ ፣ እንዲያፈራ እንዲወርስ ነበር በእግዚአብሄር የተባረከው የታጠቀውና
የተለቀቀው፡፡
እግዚአብሔርም
ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም
ሁሉ ግዙአቸው። ዘፍጥረት 1፡28
መርገም የተጀመረው ሰው እግዚአብሄር ያዘዘውን
ባለመታዘዝ የሰይጣንን ድምፅ ሰምቶ እግዚአብሄር ላይ ካመፀ በኋላ ነው፡፡
አዳምንም
አለው፦ የሚስትህን ቃል ሰምተሃልና፥ ከእርሱ እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍም በልተሃልና ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት
ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤ እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ። ወደ ወጣህበት መሬት
እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤ ዘፍጥረት 3፡17-19
ሰው
በሃጢያት ከመውደቁና በመርገም ሃይል በታች ከመውደቁ በፊት ነገሮች በቀላሉ ይሰሩለት ነበር፡፡ ሁሉም ነገር ይታዘዘው ፣ ይገዛለትና
ይተጋለትና ይሰራለት ነበር፡፡ ሰው በአመፃው ምክኒያት ሲረገም ሁሉም ነገር ለገመበት፡፡ ሁሉም ነገር እንደአቅሙ መጠን አልሰጥም
አለው፡፡
ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይልዋን አትሰጥህም፤ ዘፍጥረት 4፡12
እግዚአብሄር አብርሃምን ከጠራው በኋላ በያቆብ
ወይም እስራኤል የራሱን ህዝብ ከለየ በኋላ የእስራኤል ህዝብ የሚረገምበትንና የሚባረክበትን መንገድ አሳያቸው፡፡ በብሉይ ኪዳን መርገም
የእስራኤልን የብሉይ ኪዳን ህግ ከመጠበቅና ካለመጠበቅ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
እስራኤላዊያን የታዘዙትን መተዳደሪያ ደንባቸውን
ትእዛዙን ባይሰሙና ባያደርጉት የሚከተለው መርገም እንዳለ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡
ነገር
ግን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ሁሉ ባትጠብቅ ባታደርግም፥ እነዚህ መርገሞች
ሁሉ ይመጡብሃል ያገኙህማል። ዘዳግም 28፡15
የእግዚአብሄርን የብሉይ ኪዳን ህግ ያልፈፀሙ የእስራኤ
ህዝብ አግዚአብሄር እንደተናገረው በብዙ መርገም ውስጥ ያል ነበር፡፡
በአዲስ ኪዳን ደግሞ በአይሁድ ህግ ሲኖሩ ለነበሩ
ኢየሱስን ለተቀበሉ አይሁዳዊያን የእስራኤል ህዝብ ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሰቀል መርገም ስለሆነላቸው ከህግ እርግማን እንዳዳናቸው
ያስተምራል፡፡
በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤ ገላትያ 3፡13
በአዲስ ኪዳን በግልፅ የተቀመጠው ብቸኛው መርገም
ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ሰው የተረገመው መርገም ነው፡፡
ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። 1ኛ ቆሮንቶስ 16፡22
ምክኒያቱን
እግዚአብሄር ያዘጋጀውን የመዳኛ መድሃኒት ኢየሱስንም ያለተቀበለ ሰው አንድያ ልጁን በመስጠት እግዚአብሄር ያዘጋጀው የመዳኛ መንገስድ
ስላልተቀበለ በእግዚአብሄር ቁጣ ስር ይኖራል፡፡
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር
ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36
በልጁ በኢየሱስ የሚያምን ሰው አዲስ ፍጥረት ነው፡፡
ኢየሱስን እንደአዳኝ የተቀበለ ሰው እግዚአብሄር ተቀብሎታል፡፡ ኢየሱስን በሚከተል ሰው እግዚአብሄር ደስ ተሰኝቶበታል፡፡
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17
እርግጥ ነው ክርስትያን ከሃጢያት እና ከሃጢያት
ውጤቶች ነፃ ይወጣ ዘንድ የእግዚአብሄን ቃል መፈለግ መወቀበልና ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ተቀብሎ ባደረገው
መጠን በክርስቶስ ያለውን እጅግ አስደናቂ አርነት ይለማማዳል፡፡
ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፦ እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። ዮሃንስ 8፡31-32
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #መርገም #እርግማን #ክርስቶስ #ህይወት #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #መፀለይ #ሞገስ #በረከት #ስኬት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #እረፍት
No comments:
Post a Comment