የእናንተ ጠቦት ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ይሁን፤ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ውሰድ። በዚህም ወር እስከ አሥራ አራተኛው ቀን ድረስ ጠብቁት፤ የእስራኤልም ማኅበር ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት። ከደሙም ወስደው በሚበሉበት ቤት ሁለቱን መቃንና ጉበኑን ይቅቡት። ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ፥ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ እንዲህ ብሉት፥ ፈጥናችሁም ትበሉታላችሁ፤ እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፥ በግብፅም አገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። ደሙም ባላችሁበት ቤቶች ምልክት ይሆንላችኋል፤ ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ፤ እኔም የግብፅን አገር በመታሁ ጊዜ መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም። ዘጸአት 12፡5-7፣11-13
እስራኤላዊያን ከግብፅ ሲወጡ ያደረጉት ስርአት የአዲስ ኪዳን ምሳሌ ነበር፡፡ እስራኤላዊያን ያረዱት ጠቦት ለእኛ ሃጢያት የሞተው የኢየሱስ ምሳሌ ነበር፡፡
እስራኤላዊያን እንዲያርዱት የታዘዙት ነውር የሌለበት ጠቦት ነበር፡፡ ዘጸአት 12፡5
በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ። ዮሃንስ 1፡29
እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21
የእስራኤል ህዝብ ከሞት መቅሰፍት እንዲድኑ ደሙን በመቃናቸው ላይ እንዲረጩት ታዘዋል፡፡ ዘጸአት 12፡6
ንስሃ በመግባት በኢየሱስ ደም የታጠበ ሰው ከሞት ወደ ህይወት ተሸጋግሯል አንጂ ሞትን አያይም፡፡
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። ዮሃንስ 5፡24
በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም። ዮሃንስ 3፡36
ደሙን ባየ ጊዜ መቅሰፍት ወደቤታቸው አይገባም ነበር ያልፋቸው ነበር፡፡ ዘጸአት 12፡13
ኢየሱስን የምንከተል ሁላችን የደሙ ምልክት በእኛ ላይ ይኖራል፡፡ ማንኛውም አይነት ከህይወት የተለየ ነገር (ሞት) በእኛ ላይ ስልጣን የለውም፡፡
እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም። ራእይ 12፡11
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ጠቦት #በግ #ደም #ፋሲካ #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ማለፍ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment