ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ እንዲህ ሲል፦ በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች፦ ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር። አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ፦ ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥ ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ። ጌታም አለ፦ ዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ። እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን? ሉቃስ 18፡8
የማይፀልይ ሰው የማይፀልየው ከእግዚአብሄር የሚፈልገው ነገር ስለሌለ አይደለም፡፡ ከእግዚአብሄር የማይፈልገው ነገር የለም፡፡ የማይፀልይ ሰው አብዛኛውን ጊዜ ሰው የማይፀልየው እግዚአብሄር ስለማያስፈልገው አይደለም፡፡ ሰው ምንም ነገር ባያስፈልገው እግዚአብሄር ያስፈልገዋል፡፡
ሰው ፀልዮ ከእግዚአብሄር የማይቀበለው ፀሎት እምነት ስለሚጠይቅ ነው፡፡ ሰው ባለጠጋ አባት እያለው በጉድለት የሚኖረው ለመፀለይ ሲሰንፍ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለምኑ ፀልዩ እያለ ደጋግሞ እያስተማረ ሰው ወደ እግዚአብሄር ፀልዮ የማይቀበለው ስለማያምን ነው፡፡
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ማቴዎስ 7፡7-8
የፀሎት መልስ ለትጉሆች እንጂ ለሰነፎች አይደለም፡፡ የፀሎት መልስ ለአማኞች እንጂ ለተጠራጣሪዎች አይደለም፡፡ የፀሎት መልስ ለሚያቋርጡና ለሚረሱት ሳይሆን ሳያቋርጡ ለሚፀልዩ ነው፡፡
ጥያቄው እምነት አለ ወይ ነው፡፡ እምነት ካለ የፀሎት ጥያቄ ይመለሳል፡፡ ድል ሳያቋርጡ ለሚፀልዩ ነው፡፡
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በእግዚአብሔር እመኑ። እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። ማርቆስ 11፡22-24
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፀሎት #ፅናት #ትግስት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር
No comments:
Post a Comment