Popular Posts

Saturday, April 15, 2017

መልካም የትንሳኤ ህይወት

የትንሳኤን በዓል ማክበር አለ፡፡ የትንሳኤን ህይወት መኖር አለ፡፡
ኢየሱስ የሞተውና የተነሳው ለራሱ አይደለም፡፡ ኢየሱስ የሞተውና የተነሳው ለእኛ ነው፡፡ኢየሱስ የሞተውና የተነሳው በእኛ ምትክ ነው፡፡ ኢየሱስ የሞተውና የተነሳው ስለእኛ ነው፡፡
ኢየሱስ ሲሞትና ሲነሳ እኛም አብረነው ተነስተናል፡፡ ከኢየሱስ ጋር አብረን የተነሳን ሁላችን የትንሳኤውን ሃይል በህይወታችን እንድንለማመደው ተሰጥቶናል፡፡ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሳይ ያው ሃይል በእኛ ውስጥ ይሰራል፡፡ ሰው በጉልበቱ ክርስትናን ሊኖር አይችልም፡፡ ክርስትና የትንሳኤውን ሃይል ይጠይቃል፡፡  
ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤ ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። ኤፌሶን ሰዎች 1፡18-22
የትንሳኤን ህይወት የሚኖረው ሰው የሚታወቅባቸው ሰባት መንገዶች
1.      በትንሳኤው ሃይል የሚኖር ሰው ከሃጢያት በላይ የሆነን ኑሮ ይኖራል፡፡  
ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና። ሮሜ 6፡6
2.     በትንሳኤው ሃይል የሚኖር ሰው በሰይጣን ላይ ስልጣን አለው፡፡
እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። ሉቃስ 10፡19
3.     በትንሳኤው ሃይል የሚኖር ሰው በሃጢያተኛ ስጋ ላይ ስልጣን አለው፡፡
እንግዲህ ለምኞቱ እንድትታዘዙ በሚሞት ሥጋችሁ ኃጢአት አይንገሥ፤ ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና። ሮሜ 8፡12፣14
4.     በትንሳኤ ሃይል የሚኖር ሰው እግዚአብሄር በምድር ላይ በሰጠው ራእይ ላይ ሙሉ ስልጣን አለው፡፡
ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 2፡14
5.     በትንሳኤው ሃይል የሚኖር ሰው በሁኔታዎች ላይ ስልጣን አለው፡፡
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ሮሜ 8፡37-38
6.     በትንሳኤው ሃይል የሚኖር ሰው በመንፈሳዊ ሞት ላይ ስልጣን አለው፡፡
እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። ዕብራውያን 2፡14-15
7.     በትንሳኤ ሃይል የሚኖር ሰው ስጋዊ አካሉ በመንፈሱ ሃይልን ያገኛል፡፡
ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ ክርስቶስ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በእናንተ በሚኖረው በመንፈሱ፥ ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል። ሮሜ 8፡11
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ህይወት #ትንሳኤ #ሃይል #ስልጣን #ፋሲካ #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ  #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment