አዝ፦ ተነሥቷል (2x)
፡ የመቃብር
፡ ደጃፍ
፡ ተከፍቷል
ድንጋዩ ፡ በሩቅ ፡ ተንከባሏል
ከፈኑ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አስክሬኑ
፡ የታል?
በእውነትም ፡ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሥቷል
(2x)
ኢየሱስ ፡ ማሸነፉን
፡ ይስማ
፡ ኢየሩሳሌም
ይውጣ ፡ ምሥራቹ ፡ ከዓለም ፡ እስከዓለም
ይስማኝ ፡ ጠላትም ፡ መርዶውን
፡ አልቅሶ
ጌታ ፡ እንደው ፡ ተነስቷል
፡ አይሞት
፡ ተመልሶ
አዝ፦ ተነሥቷል (2x)
፡ የመቃብር
፡ ደጃፍ
፡ ተከፍቷል
ድንጋዩ ፡ በሩቅ ፡ ተንከባሏል
ከፈኑ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አስክሬኑ
፡ የታል?
በእውነትም ፡ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሥቷል
ይወገድ ፡ ድንጋዩ ፡ ጠባቂውም
፡ ይምጣ
ኢየሱስን ፡ ካቃተው ፡ ጌታ ፡ መውጫ ፡ ካጣ
የትኛው ፡ ጠባቂ ፡ ነው ፡ የከለከለው
ጌታ ፡ መቃብሩን
፡ ሲፈነቃቅለው
አዝ፦ ተነሥቷል (2x)
፡ የመቃብር
፡ ደጃፍ
፡ ተከፍቷል
ድንጋዩ ፡ በሩቅ ፡ ተንከባሏል
ከፈኑ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አስክሬኑ
፡ የታል?
በዕውነትም ፡ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሥስቷል
ይነገር ፡ ለዓለም ፡ ምስራች ፡ ይሰማ
ሞትን ፡ አሸንፏል
፡ ጀግናው
፡ ኢየሱስማ
ይህ ፡ ሐሰት ፡ አይደለም
፡ ዘለዓለም
፡ እውነት
፡ ነው
ይታይ ፡ የጌታችን
፡ መቃብር
፡ ባዶ
፡ ነው
አዝ፦ ተነሥቷል (2x)
፡ የመቃብር
፡ ደጃፍ
፡ ተከፍቷል
ድንጋዩ ፡ በሩቅ ፡ ተንከባሏል
ከፈኑ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አስክሬኑ
፡ የታል?
በእውነትም ፡ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሥቷል
ይሄ ፡ ነው ፡ እንግዲህ
፡ የጐልጐታው
፡ ሚስጥር
ወንጌላችን ፡ ኢየሱስ ፡ ከሙታንም
፡ በኩር
ሙትን ፡ አናመልክም
፡ መቃብር
፡ የዋጠ
ያሸነፈን ፡ እንጂ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ የነሳ
አዝ፦ ተነሥቷል (2x)
፡ የመቃብር
፡ ደጃፍ
፡ ተከፍቷል
ድንጋዩ ፡ በሩቅ ፡ ተንከባሏል
ከፈኑ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አስክሬኑ
፡ የታል?
በእውነትም ፡ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሥቷል
መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን
No comments:
Post a Comment