Popular Posts

Follow by Email

Wednesday, April 12, 2017

በኢየሱስ ሞት የተፈፀሙ ሶስት ነገሮችና ትርጉማቸው

ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሞተበት ጊዜ ሶስት ታላላቅ ትርጉም ያላችው ሁኔታዎች ተፈፅመዋል፡፡  
1.      የቤተመቅ ደስ መጋረጃ ተቀደደ
ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ። እነሆም፥ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፥ ምድርም ተናወጠች፥ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤ ማቴዎስ 27፡50-51
እግዚአብሄር ቅዱስ ነው፡፡ በሃጢያት ምክኒያት ሰው ወደ እግዚአብሄር መግባት አይችልም ነበር፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያታችን እዳ ሙሉ ለሙሉ ስለከፈለ እግዚአብሄርና ሰው መለያየት ቀረ፡፡ ሰው በኢየሱስ በኩል ወደ እግዚአብሄር መግባት ተሰጠው፡፡
እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥ ዕብራውያን 10፡19-20
2.     ቅዱሳን ከሞት ተነሱ
መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤ ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ። ማቴዎስ 27፡52-53
ኢየሱስ ስለሃጢያታችን እዳ በመስቀል ላይ ስለሞተ በኢየሱስ ያመንም ሁላችን አሁን በትንሳኤ ህያው እንደሆንን ያሳያል፡፡
ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ ኤፌሶን 2፡5
3.     የኢየሱስንም የእግዚአብሄር ልጅነት የማያምኑ መሰከሩ
ስድስት ሰዓትም ያህል ነበረ፥ ጨለማም እስከ ዘጠኝ ሰዓት በምድር ሁሉ ላይ ሆነ፥ ፀሐይም ጨለመ፥ ሉቃስ 23፡44
የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው፦ ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ ብለው እጅግ ፈሩ። ማቴዎስ 27፡54
የምድር መናወጥና በቀን ጨለማ ሆነ፡፡ ተፈጥሮ እንኳን ስለኢየሱስ ሞት መልስን ሰጠች፡፡ የኢየሱስ መሞት ዋናው አላማ ሰዎች በስሙ አምነው ከሃጢያታቸው እንዲድኑ ነው፡፡
እንዲህም አላቸው፦ ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል። እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ። ሉቃስ 24፡46-48
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #መስቀል #ስቅለት #ጠቦት #መጋረጃ #ደም #ትንሳኤ #ሞት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ተፈፀመ #ቤተመቅደስ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment