የእስራኤል
ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ ኢሳይያስ 30፡15
እግዚአብሄር
እንዲሰራ ሰው ሊያርፍ ያስፈልጋል፡፡ ሰው ካላረፈ እግዚአብሄር ወይም አይሰራም ቢሰራም ደግሞ እግዚአብሄ እንደሰራ አያስታውቅም፡፡
ሰው ካላረፈ እግዚአብሄር ብቻውን ክብሩን ሊወስድ አይችልም፡፡ ሰው ካላረፈ የሰውና የእግዚአብሄር ክብር ይደባለቃል፡፡
ሰው
በእረፍት ሆኖ እግዚአብሄር ሲሰራ ብቻ ነው ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሄር ክብሩን መስጠት የሚችለው፡፡ ሰው ሳያርፍ ምንም ነገር ቢሆንለት
እንኳን "እግዚአብሄር ረድቶኛል እኔም ግን ቀላል ሰው አይደለሁም" ነው የሚለው፡፡
እግዚአብሄር እንድንሰራ እንኳን የሚፈልገው በእረፍት ነው፡፡ ስራችንነን እንኳን
አንድንጀምር የሚፈልገው በእርሱ ካረፍን በኋላ ነው፡፡ ከስራ በፊት አንኳን መጀመሪያ በእርሱ እንድናርፍ ይፈልጋል፡፡
ለእግዚአብሄር
ምንም ነገር ካደረግንለት እግዚአብሄር አስቀድሞ ሰርቶ እንደጨረሰው በማመን መሆን አለበት፡፡ ወደምድር የመጣነው እንኳን እግዚአብሄር
አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ስራ ለመስራት እንጂ ለስራ ፈጠራ አይደለም፡፡ ስለዚህ ከመስራታችን በፊት በእግዚአብሄር ዘንድ አንደተሰራ
አውቀን በምድር ላይ ለማስፈፀም ብቻ እንደሆነ ማወቅ ይገባናል፡፡
ዓለም
ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን። በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ
ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን። በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ። ኤፌሶን
1፡4-6
ለእግዚአብሄር
ምንም ከማድረጋችን በፊት እንድናርፍ መፈለጉ ብቻ ሳይሆን በስራ መካከል እንድናርፍ ይፈልጋል፡፡
ስንሰራም
በእረፍት እንድንሰራ ነው እግዚአብሄር የሚፈልገው፡፡ ሳናርፍ የምንሰራውን ምንም ነገር እግዚአብሄር አይፈልገውም፡፡ ስለፀሎት አንኳን
መፅሃፍ ቅዱስ ሲናገር ሳትለምኑት ምን እንምደሚያስፈልጋችሁ ያውቃል ነው የሚለው፡፡
አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ
አትድገሙ። ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና። ማቴዎስ 6፡7-8
ስለዚህ ስንፀልይ እንኳን አዲስን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ልንቆረቁር እንደሆነ ሊሰማን
አይገባንም፡፡ በእውነት የእግዚአብሄርን ስራ ለመስራት ከፈለግን አስቀድሞ የተሰራውን ስራ መከተል ብቻ ነው፡፡
ሰለዚህ ነው ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ አባቴ ይሰራል እኔም እሰራለሁ
በማለት ከእግዚአብሄር ጋር አብሮ እነደሚሰራ የሚናገረው፡፡
ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው።
ዮሃንስ 5፡17
እግዚአብሄር በትጋት እየሰራ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚሰራውን ነገር ተረድተን ከእርሱ
ጋር አብረን መስራት ከሁሉም የሚበልጥ የተሻለ ነገር ነው፡፡
በማረፍ ከብክነት እንድናለን፡፡ በማረክ አግዚአብሄር በማይዘራበት እንዳንዘራ እንጠበቃለን፡፡
በማረፍ እግዚአብሄር በሌለበት እንዳንሰራ እንጠበቃለን፡፡ በማረፍ ከከንቱ ድካም እንድናለን፡፡
እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥
ጠባቂ በከንቱ ይተጋል። በማለዳ መገሥገሣችሁም ከንቱ ነው። ለወዳጆቹ እንቅልፍን በሰጠ ጊዜ፥ እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥
ከተቀመጣችሁበት ተነሡ። መዝሙር 127፡1-2
የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤
በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ ኢሳይያስ 30፡15
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እረፍት #ቅድሚያ #እምነት #መደገፍ #ሰንበት #ማረፍ #ፅድቁን #ኢየሱስ #ክርስቶስ
#ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ፀጥታ #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #መታመን #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment