ለምኑ፥
ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥
የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ማቴዎስ 7፡7-8
መፅሃፍ
ቅዱስ "መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው" (ዮሐንስ
1፡18) እንደሚል የእግዚአብሄርን ልብ የምናውቀው ከእግዚአብሄር ተልኮ በመጣው በኢየሱስ ንግግርና ትምህርት ነው፡፡
ኢየሱስ
በምድር በተመላለሰበት ጊዜ ሰዎች ከእግዚአብሄር ፀልየው እንዲቀበሉ በተደጋጋሚ አስተምሮዋል አበረታቷል፡፡
ኢየሱስ
የእግዚአብሄርን ሁሉን ቻይነትም ያውቀዋል፡፡
ኢየሱስ
የእግዚአብሄርን ባለጠግነት ያውቀዋል፡፡
ለሚጠሩትም
ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ ሮሜ 10፡12
ኢየሱስ
የእግዚአብሄርን ደግሞ መልካምነት ፣ ርህራሄውንና ፈቃደኝነቱን ያውቀዋል፡፡
ወይስ
ከእናንተ፥ ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው? ዓሣስ ቢለምነው እባብን ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ
ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን
ይሰጣቸው? ማቴዎስ 7፡9-11
የሰዎችን
ሁኔታ ሲመለከት ከእግዚአብሄር ለምነው መቀበል ያለባቸ ብዙ ነገሮች እንዳለ በማየቱ የእግዚአብሄር ባለጠግነት ወደሰዎች በፀሎት አንዲተላለፍ
በታላቅ ቅናት በተደጋጋሚ ስለ ፀሎት አስተምሮዋል፡፡
እውነት
እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን
ለምኑ ትቀበሉማላችሁ። ዮሃንስ 16፡23-24
ኢየሱስ
በእምነትም የሚለምን ሁሉ የሚለምንውን ነገር ሁሉ ከእግዚአብሄር እንደሚቀበል አስተምሮዋል፡፡
አምናችሁም
በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ አላቸው። ማቴዎስ 21፡22
ለምኑ፥
ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ማቴዎስ 7፡7-8
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፀሎት #አማርኛ #ለምኑ #ፈልጉ
#መፅሃፍቅዱስ #አንኳኩ #መልካምእግዚአብሄር #ቃል #አእምሮ #ማደስ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment