የሰው አካሄድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይጸናል፥ መንገዱንም ይወድዳል። መዝሙር 37፡23
ሰውን እግዚአብሄር የፈጠረው ለክብሩ ነው፡፡ እግዚአብሄር በእያንዳንዱ የህይወት ክፍላችን ውሰጥ ሙሉ ለሙሉ ይካተታል፡፡ እግዚአብሄር የህይወታችን ዝርዝር ነገሮች ሁሉ ግድ ይሉታል፡፡
አምስት ድንቢጦች በአሥር ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ስንኳ በእግዚአብሔር ፊት አትረሳም። ነገር ግን የእናንተ የራሳችሁ ጠጕር ሁሉ እንኳ የተቈጠረ ነው፤ እንግዲያስ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች ትበልጣላችሁ። ሉቃስ 12፡6-7
እግዚአብሄር የፈጠረን በአላማ ነው፡፡ ወደ ምድር ከመምጣታችን በፊት የተዘጋጀ የምንሰራው መልካም ስራ አለ፡፡ ወደ ምድር የመጣነው እግዚአብሄር አስቀድሞ ያየልንን መልካም ስራ ለመስራት ነው፡፡
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ኤፌሶን 2፡10
እግዚአብሄር ለእድል የሚተወው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገውን ያውቃል፡፡ የሚታዘዘውና ራሱን የሚሰጠው ካገኘ ደግሞ በትጋት ይሰራዋል፡፡
ስለዚህ ነው እግዚአብሄር የሰውን አካሄድ በትጋት የሚመራው፡፡ እግዚአብሄር እንዲመራን ከምንፈልገው በላይ እግዚአብሄር ሊመራን ይፈልጋል፡፡
የሰው አካሄድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይጸናል፥ መንገዱንም ይወድዳል። ቢወድቅም ለድንጋፄ አይጣልም፥ እግዚአብሔር እጁን ይዞ ይደግፈዋልና። መዝሙር 37፡23-24
የእግዚአብሄርንም መንገድ ፈልጎ አካሄዱ የማይፀና ሰው የለም፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ያድርጉ!
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #አካሄድ #እርምጃ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መናገር #መንገድ #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment